ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ በታላቁ ሩጫ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል 12ቱ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር በሚል መታሰራቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15/2016 ዓ.ም፡- ባላፈው ሳምንት እሁድ ህዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው ታላቁ ሩጫ ተሳታፊ የነበሩን መፎክር ሲያሰሙ ከነበሩት መካከል 12 የሚሆኑን ለእስር መዳረጋቸው ተገለጸ።

የእሩጫው ተሳታፊዎች ለእስር የተዳረጉት በአዲስ አበባ ውስጥ ኹከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር አስባችኋል፣ እንዲሁም ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ንግግር አድርጋችኋል በሚል መሆኑን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ በነጻ ጥብቅና ከቆሙላቸው የህግ ጠበቃ የሆኑትን ሰለሞን ገዛኸኝ መስማቱን በዘገባው አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹን ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሶስተኛ ፖለስ ጣቢያ ውስጥ በአካል እንዳገኟቸው እና በነፃ ጥብቅና እንደሚቆሙላቸው እንደገለፁላቸው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ነግረውኛል ያለው ዘገባው ከ12ቱ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ሌሎች ሦስት ወጣቶች ተይዘው እንደነበር እና ከምርመራ በኋላ መለቀቃቸውን መስማታቸውን ገልጸውልኛል ብሏል።

በተመሳሳይ ሰለሞን አላምኔ የተባሉ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል «ከታላቁ ሩጫ ጋር ተያይዞ ውድድሩ ከመካሄዱ አስቀድሞ ሩጫው ላይ ኹከት እና ብጥብጥ ሊፈጥሩ ይችላል ከሚል ሥጋት» ተጠርጥረው መያዛቸውንና ፍርድ ቤት ቀርበው የአሥር ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ፓርቲው መግለጹን ዘገባው አመላክቷል።

ሩጫው እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ከተሰሙ መፈክሮቹ መካከል አዲስ አበባን የሚመለከተው እና «እየመጡ ነው» የሚለው ይገኝበታል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button