ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል ለ50 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የሙያ ብቃት ፈተና ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17/2016 ዓ.ም፡- የኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ በዘንድሮው ዓመት ለ50 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ለመስጠት ማቀዱንና እስካሁን ለ12 ሺህ 50 ሠራተኞች መስጠቱን አስታወቀ።

በተያዘው ዓመት ለ50 ሺህ የክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ለመስጠት አቅዶ እስካሁን ለ12 ሺህ 50 ሠራተኞች ፈተናውን ሰጥቷል ሲሉ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።

የአንድን ሠራተኛ ብቃት ለመለካት ፈተናው ብቻውን በቂ ስለማይሆን ሌሎች ተጨማሪ የመመዘኛ መስፈርቶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ ሲሉም አስረድተዋል ያለው ዘገባው እስካሁን ባለው ሁኔታ በኦሮሚያ አንድን የመንግሥት ሠራተኛ ለመመዘን ፈተናው 25 በመቶ ክብደት የሚይዝ ሲሆን ትልቁ ክብደት ማለትም 75 በመቶ የሚይዘው ግን የሥራ ልምድ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ አፈጻጸምና ሥነ ምግባር ነው ማለታቸውን አስታውቋል።

በተለይ የሥራ ልምድ ብቻውን 22 በመቶ ክብደት አለው ማለታቸውነ ጠቁሟል።

በፈተናው ማለፊያ ውጤት ያላመጣ ሠራተኛ ራሱን እንዲያበቃ ከደረጃው ዝቅ ብሎ ይመደባል ያሉት ምክትል ኃላፊው ሆኖም ከሥራ ገበታ ይባረራል ተብሎ የሚናፈስ ወሬ መሠረተ ቢስ ነው ብለዋል።

በክልሉ ቀደም ብሎ ስለ ፈተናው ዓላማ በቂ ግንዛቤ ስለተሰጠ እስካሁን ያጋጠማቸው ችግር አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ሠራተኞችም በፈተናው ደስተኛ መሆናቸው ባደረጉት የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

ለኦሮሚያ ለሠራተኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት አዲስ ክስተት እንዳልሆነ ያወሱት አቶ ያዕቆብ፤ በኦሮሚያ በ2011 ዓ.ም በወጣው የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ሕግ ፈተናው እንዲሰጥ በጨፌ ኦሮሚያ መጽደቁን ጠቁመዋል። ፈተናው ስኬታማ እንዲሆንም የኦሮሚያ መንግሥት ዩኒቨርስቲ የአንበሳውን ድርሻ እየተጫወተ ነው ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከፈተናው በተጓዳኝ ቢሮው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የማጣራት ሥራ እያከናወነ ይገኛል ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ ከፌዴራል ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ጋር በመሆን ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዲግሪና ከዚያ በላይ የተመረቁ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ እየተሠራ ነው።

በመቀጠልም ከመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ የሠራተኞች ማስረጃ የማጣራት ሥራ ይጀመራል ብለዋል። እስካሁን ባለው ሥራ የስምንት ሺህ ሠራተኞች ማስረጃ ከ24 መሥሪያ ቤቶች፣ ከአምስት ዞኖችና ከሁለት ከተማ መስተዳድሮች መሰብሰቡንም ገልጸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button