ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በምርት ዘመኑ በዋና ዋና ሰብል 513 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት የተያዘው ዕቅድ ይሳካል ሲል ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24/2016 ዓ.ም፡- በ2015/2016 ምርት ዘመን በዋና ዋና ሰብል 513 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት የተያዘው ዕቅድ እንደሚሳካ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዘር የተሸፈነው የእርሻ መሬት የተሸለ ከመሆኑም ባሻገር የተሻለ የዝናብ ስርጭት እና የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም መኖራቸው ለስኬቱ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የግብርና ሚኒስቴር በማህበራዊ የፌስቡክ የትስስር ገጹ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ያጋራው መረጃ እንደሚጠቁመው የሰሞኑ ፀሓያማ የአየር ሁኔታ የደረሱ ሰብሎችን በአግባቡ ለመሰብሰብ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን የሚኒስቴሩ የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢሳያስ ለማ መናገራቸውን አስታውቋል፡፡

አሁንም አርሶ አደሮች፣ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው የሕብረተሠብ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራሩን አጠናክረው በመቀጠል የደረሱ ሰብሎችን በጊዜ ሰብስበው በጥንቃቄ ወደ ጎተራ ማስገባት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን መረጃው አካቷል።

ዘንድሮ በሀገር ደረጃ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 117 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት የታቀደውን ለማሳካት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በአግባቡ እንዲያበረክቱ ስራ አስፈጻሚው መጠየቃቸውንም አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button