ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በሳዑዲ አረብያ የሚቀጠሩ ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች ወርሃዊ ክፍያ በአንድ ሺ ሪያል እንዲቀንስ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9/2016 .ም፡ የሳኡዲ አረብያ መንግስት በሀገሪቱ በቤት ሰራተኝነት የሚቀጠሩ ኢትዮጵያውያን ወርሃዊ ደመወዝ በአንድ ሺ የሀገሪቱ ገንዘብ ሪያል እንዲቀንስ ማድረጉን ገልፍ ኒውስ በድረገጹ አስነብቧል።

ኢትዮጵያውያኑ የቤት ሰራተኞች ይከፈላቸው የነበረው ዝቅተኛው ወርሃዊ ክፍያ 6900 የሀገሪቱ ገንዘብ ሪያል የነበረ ሲሆን ቅናሽ በተደረገበት ዝቅተኛው ወርሃዊ ክፍያ 5900 ሪያል መሆኑን አመላክቷል።

የሳኡዲ አረብያ የሰው ሃብት እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ በተጨማሪ የአምስት ሀገራት ተቀጣሪዎች ማለትም የፊሊፒንስ፣ ሲሪላንካ፣ ባንግላዴሽ፣ ኡጋንዳ እና ኬንያ ዜጎች የቤት ሰራተኞችም ቅናሽ የተደረገበት ክፍያ ይመለከታቸዋል።

15ሺ 900 ይከፈላቸው የነበሩ ፊሊፕናውያን የቤት ሰራተኞች በአዲሱ ዝቅተኛ ወርሃዊ ክፍያ 14ሺ 700 ሪያል እንዲከፈላቸው መወሰኑን ያስታወቀው የሀገሪቱ መንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የኬንያውያን የቤት ሰራተኞችም ይከፈላቸው ከነበረው 10ሺ 870 ሪያል ወደ 9ሺ ሪያል ዝቅ መደረጉን ጠቁሟል።

የሀገሪቱ መንግስት የቤት ሰራተኞቹ ወርሃዊ ክፍያ ዝቅ እንዲል የተደረገው የቤት ሰራተኞችን አመላመል እና ክፍያ ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት አካል መሆኑን ገልጿል።

በኢትዮጵያ በመንግስት እውቅና ተችሮት በፌስቡክ በተካሄደ ዘመቻ ወደ ሳዑዲ አረብያ የቤት ሰራተኞች ቅጥር መፈጸሙ ለህገወጥ አዘዋዋሪዎች፣ የጉልበት ብዝበዛ ፈጻሚዎች ግፍ ለመፈጸም የሚያስችል ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል ሲል ግሎብ ኤንድ ሜይል ድረገጽ ባሰራጨው ዘገባ ማጋለጡን መዘገባችን ይታወሳል።

በቤት ሰራተኛ መልማይ ኤጀንሲ ቅጥር ፈጽማ ወደ ሳዑዲ አረብያ በመጓዝ በስራ ላይ የነበረች ፍቅርተ የተባለች ኢትዮጵያዊት ታሪክን በአብነት ያስነበበው ድረገጹ ከአዲስ አበባ ወደ ሳዑዲ አረብያ ያቀናቸው ፍቅርተ አሰሪዎቿ ምንም አይነት ምግብ ሳይሰጧት በረሃብ በርካታ ሳምንታት አድካሚ ስራ ሲያሰሯት ከቆዩ በኋላ ምንም አይነት ክፍያ ሳይፈጽሙላት ደካማ ናት ብለው ለኤጀንሲው እንደመለሷት አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button