ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል ባለው የትጥቅ ግጭት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት መደረሱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ባለፉት ወራት እየተካሄደ ባለው የትጥቅ ግጭት፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ላይ በታጣቂ ቡድን በደረሰ ውድመት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ። 

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊና የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ትላንት በሰጡት መግለጫ ውድመቱ በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡንም ገልጸዋል።

አቶ ደሳለኝ ጣሰው፤ “ፅንፈኛው ቡድን” ሲሉ የጠሯቸው አካላት፤ “ህዝቡን በመዝረፍና ሰዎችን በማገት ላይ መሆናቸውን” ገልጸዋል። “መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገባውን ማዳበሪያ ሳይቀር እየዘረፉ ለግል ጥቅሙ እያዋሉ ነው” ሲሉ አክለው ገልጸዋል። 

“ቡድኑ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ህዝቡን ለተደራራቢ ችግር እየዳረገ እንደሚገኝም” ጠቅሰው፤ ይህንን “ከህዝብ ጥቅም በተቃራኒ” የሆነ ተግባር የሚፈጽመውን  ህዝቡ አምርሮ ሊታገለው ይገባል ብለዋል።

የህዝብን ጥቅም አስጠብቃለሁ ብሎ የሚታገል አካል “ህዝብን ሊዘርፍና ሊቀማ” ፈጽሞ አይችልም ያሉት አቶ ደሳለኝ፤ ይህንን የአማራ ክልል ህዝብ እሴት ያልሆነ ተግባር መታገልና ማስቆም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በክልሉ መንግስት በተደረገ የሰላም ጥሪና በህግ ማስከበር ወቅት ስራ በቁጥጥር ስር የዋሉ ከ10 ሺህ 500 በላይ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል።

ባለፉት ቀናት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ዳግም ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሷል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ከተማ ሃሙስ የካቲት 21/ 2016 ዓ/ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ተካሄዷል

ከሁለት ሳምንታት በፊት በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በተቀሰቀሰው ግጭት መንገዶች ተዘግተዋል።  

በጎንደር፣ መራዊ፣ ደጋ ዳሞት፣ ሸዋ ሮቢት፣ አንጾኪያና ገምዛ እና ላሊበላ በመሳሰሉት ከተሞች አካባቢ ከባድ ውጊያዎች ተካሄደዋል። 

አቶ ደሳለኝ በመግለጫቸው የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የፀጥታ አካላት በጋራ በመሆን “ፅንፈኛ ቡድኑ” ጥፋት ለመፈፀም ያደረገውን ሙከራ ማክሸፍ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት “የተገኘውን ሰላም በማፅናት ህግ የማስክበር ስራውን የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም” አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button