ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል ባለው ግጭት 967 የጤና ተቋማት መዘረፋቸው እና በ298 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መደረሱ ተገለጸ 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂ ቡድኖች መካከል እያተካሄደ ባለው ግጭት፤ 967 የጤና ተቋማት መዘረፋቸው እና በ298 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መደረሱ ተገለጸ። 

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱል ከሪም፤ በስም ያለጠሯቸው ነገር ግን “የክልሉን ሕዝብ ጥያቄ እናስመልሳለን በሚል ሰበብ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ቡድን” ያሏቸው አካላት፤  “በክልሉ 967 የጤና ተቋማትን ዘረፈዋል” ሲሉ ከሰዋል።

አብዱል ከሪም፤ ታጣቂዎቹ “የክልሉን ሕዝብ የጤና መሠረተ ልማት አውድመዋል፤ መድኃኒቶችን ዘርፈዋል፤ አንቡላንሶችንም ነጥቀዋል” ሲሉ ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። 

“በክልሉ በአጠቃላይ 124 አንቡላንሶች ከአሽከርካሪዎች እጅ ላይ በታጣቂዎች ተነጥቀው ለግጭት ዓላማ እየዋሉ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

ቢሮ ኀላፊው፤ በክልሉ ያለው ግጭት በእናቶች ጤና አገልግሎት ላይ ጫና ማሳደሩንም ገለጸው፤ የጤና ክትትል ማድረግ ከነበረባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ውስጥ 36 በመቶ የሚኾኑት ከክትትል ውጭ ናቸው ብለዋል።

በጤና ተቋማት ውስጥ መውለድ ካለባቸው እናቶች ውስጥም 44 በመቶ የሚኾኑ ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ በቤት ውስጥ እንዲወልዱ ተገድደዋል ነው ያሉት። ይህም በእናቶች ላይ ዘርፈ ብዙ የጤና ምስቅልቅል እያስከተለ ስለመኾኑ በመግለጫቸው አመላክተዋል።

ግጭቱ በሕጻናት ጤና ላይም አደጋ መደቀኑን የገለጹት ኃላፊው፤  በክልሉ 14 በመቶ የሚኾኑ ሕጻናት የጀመሩትን ተከታታይ ክትባት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል ብለዋል። ይህም የሕጻናትን እና የጨቅላ ሕጻናትን ጤና በእጅጉ የሚጎዳ ስለመኾኑ አመላክተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይህ በእንዲህ እያለ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ በተከሰተው ግጭት እና የሰላም መደፍረስ ምክንያት ”ጽንፈኛው ኀይል” ሲሉ በጠሯቸው አካላት 298 ትምህርት ቤቶች በከፊል እና ሙሉ ሙሉ ጉዳት ደርሶባቸዋል”  ብለዋል።

”ትምህርት ቤቶችን ማረፊያ በማድረግ እና ወንበሮቹንም በማቃጠል የትምህርት ቤቶቹን ቁሳቁስ እና የሰብል ምርትም ወስዷል” ሲሉ ተናግረዋል።  ተማሪዎች የጥይት ድምጽ እየሰሙ እየተሳቀቁ ስለመኾናቸውም የገለጹት ኃላፊዋ፤  በዚህም በተማሪዎች እና በትምህርት ማኅበረሰቡ ላይ ትልቅ የሥነ ልቦና ጫና መፍጠሩ ተናግረዋል።  

የመማር ማስተማሩ ሥራ እንቅፋት እየገጠመው መኾኑን  ሲገልጹም፤  በክልሉ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪ ለማስተማር ታቅዶ እስካሁን 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ያልተመዘገቡ እና ወደ ትምህርት ያልገቡ ስለመኾናቸው አስረድተዋል፡፡  ቢሮ ኀላፊዋ ተማሪዎች ብቻ ሳይኾኑ መምህራን እና የአሥተዳደር ሠራተኞችም ከሥራ ውጪ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡ በትምህርት ላይ ያሉትም ቢኾኑ በግጭቱ ምክንያት የትምህርት አሰጣጡ የተዘበራረቀ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

ግብዓት በማሟላት በኩልም በመኪና እጥረት፣ “በጽንፈኛ ኀይሉ መዘረፍ እና መታገት”  የመጻሕፍት ስርጭቱ እንቅፋት እንዳጋጠመው የጠቀሱት ኀላፊዋ በግጭቱ 3 ሺህ 500 የአንደኛ ደረጃ እና 225 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አልተከፈቱም ብለዋል፡፡ ችግሮቹ በሁሉም ዞኖች ቢኖሩም በሸዋ እና በጎጃም አካባቢዎች ደግሞ የከፋ እንደኾነ ኀላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

መምህራን ያጋጠመውን ችግር ተገንዝበው አንጻራዊ ሰላም ባለበት ፈጥነው ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ እና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ስለኾነም ሕዝቡ እና የሃይማኖት ተቋማት በግጭት እና በጦርነት የሚመለስ የሕዝብ ጥያቄ እንደሌለ በማስገንዘብ ትውልድን ለመገንባት እንዲሠሩ እና እንዲተባበሩ ጠይቀዋል፡፡

በአማራ ክልል መንግስት ባለፉት ወራት እየተካሄደ ባለው የትጥቅ ግጭት፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ላይ በታጣቂ ቡድን በደረሰ ውድመት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል

ግጭቱ  ከ1 ሺህ 500 በላይ  የውኃ ተቋማት ላይ ባደረሰው ውድመት ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት መደረሱን የክልሉ ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ገልጿል። በዚህም የተነሳ  817 ሺህ የሚኾኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግር ውስጥ ናቸው ተብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button