ዜናማህበራዊ ጉዳይህግ እና ፍትህ

ዜና፡ በአዲስ አበባ የፖሊስ አመራሮችን ጨምሮ ከ5500 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23/2016 .ም፡ በአዲስ አበባ ከተማ የፌደራል ፖሊስ እና የከተማዋ ፖሊስ በጋራ ባካሄዱት የሁለት ዙር ኦፕሬሽን የፖሊስ አመራሮችን ጨምሮ ከ5 ሺህ 536 በላይ በተለያዩ የወንጀል ተግባራት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

ፖሊስ በቁጥጥር ስር ባዋላቸው ላይ ምርመራ እያካሄደባቸው እንደሚገኝ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ የፌስቡክ የትስስር ገጹ ያጋራው መረጃ እንደሚያሳየው ኦፕሬሽኑን የመሩት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል መሆናቸውን አመላክቷል።

በቁጥጥር ስር የዋሉትም አፈና በማካሄድ በግዲያ ወንጀል የተጠረጠሩ፣ በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ የተደገፈ የዘረፋ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተጠርጣሩ ግለሰቦች ናቸው ያለው መረጃው በኦፐሬሽኑም 26 ሽጉጦች፣ 73 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ፣  በወንጀል ተባባሪ በመሆን የተጠረጠሩ የሜትር ታክሲዎች፣ እንደሚገኙበት ጠቁሟል።

ከፖሊስ ተቋምም በእነዚህ ወንጀሎች ላይ ተሳትፈው የተገኙትን አመራርና አበላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ መግለጫው አክሎ ገልጿል።

በቀጣይም ኅብረተሰቡን ባማረሩ ወንጀሎች ላይ የሚካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

በመዲናዋ ከታኅሣስ 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኦፕሬሽን መካሄዱን ያወሳው የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ በዚህ ወቅትም ከ1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች ከበርካታ ልዩ ልዩ ኤግዚቢቶች ጋር በቁጥጥር ሥር  መዋላቸውን እና በየጊዜው የደረሱበትን ውጤት እየገመገሙ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል መግባቱንም አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button