ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በህግ የበላይነት ምዘና ከአምናው ዝቅ በማለት ከ142 ሀገራት 129ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14/ 2016 ዓ.ም፦ የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP)  ዛሬ ጥቅምት 14 ባወጣው የ2023 የህግ የበላይነት ምዘና ኢንዴክስ፤ የኢትዮጵያ የህግ የበላይነት ምዘና ውጤት በዚህ አመት ከአምናው ዝቅ በማለት ከአለማችን 142 ሀገራት 129ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አስታወቀ፡፡ 

የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ባደረገው የህግ የበላይነት ምዘና ኢትዮጵያ በአህጉር ደረጃ ከ34 የሰሃራ በታች ሀገራት አራቱን ብቻ በመብለጥ 30ኛ ደረጃን ይዛለች ብሏል፡፡ ከአፍሪካ ከ42 አገራት 41ኛ በመሆን የተሻል አፈጻጸመ ያስምዘገበችው ርዋንዳ ሰትሆን ናሚቢያ እና ሞሪሺየስ 2ኛና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

ስብዓዊ መብትን፣ ፍትህ ማግኘት፣ ሙስናና አምባገነናዊትን የፈተሸው ተቋሙ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው18 ሀገራት ኢትዮጵያ 15ኛ ደረጃ ላይ ናት ብሏል። በተጨማሪም ኢትዮጵያን ጨምሮ በዚህ አመት በተሰራ ጥናቱ በተከናወነባቸው ሀገራት የህግ የበላይነት በ59 በመቶ ቀንሷል ነው ያለው።

ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድንና ጀርመንን በማስከተል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ሀገር ዴንማርክ ስትሆን ቬንዘዌላ፣ካምቦዲያ፣ አፍጋኒስታን፣ሃይቲና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊከ ኮንጎ ዝቀተኛ ደረጃን መያዛቸው ተገልጧል።

አመና ኢትዮጵያ ከአለማችን 140 ሀገራት 123ኛደረጃ፣ ከሰሃራ በታች ካሉ 34 ሀገራት 27ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ይታወሳል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button