ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በጋምቤላ ተጠልለው የሚገኙ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች በረሃብ ሳቢያ እየሞቱ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/2016 .ም፡ በጋምቤላ ተጠልለው የሚገኞ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች በረሃብ እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሳቢያ እየሞቱ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በትንሹ 30 ስደተኞች መሞታቸውን የጠቆመው ኮሚሽኑ በአፋጣኝ በቂ የተመጣጠነ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብላቸው ጠይቋል።

የጋምቤላ ክልል 400ሺ የሚጠጉ ስደተኞችን አስጠልሎ እንደሚገኝ የጠቆመው የኮሚሽኑ መግለጫ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ወዲህ የምግብ እርዳታ አቅርቦት መቋረጡን አስታውቋል። ስደተኞቹ ምግብ ፍለጋ መጠለያ ካምፓቸውን ጥለው በሚወጡበት ስአት ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው የምግብ እርዳታ አቅርቦቱ መቋረጡ ለስደተኞቹ ሞት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጾ በተጨማሪም በስደተኞቹ እና በአከባቢው ነዋሪዎች መካከል ያለውን ቅራኔ በማስፋት አከባቢው እንዳይረጋጋ ያደርጋል ሲል ስጋቱን አጋርቷል።  

በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ሁኔታ አሳሳቢ ነው ያለው ኮሚሽኑ በመግለጫው በተለይም የምግብ እርዳታ አቅርቦቱ በመቋረጡ ምክንያት ሁኔታዎች እየተባባሱ እንደሚገኙ አመላክቷል።   

ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ እና የመንግስታቱ ድርጅት የምግብ ፕሮግራም የምግብ እርዳታ አቅርቦቱን ለማስቀጠል እንዲጥሩ አሳስቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button