ዜናቢዝነስ

ዜና፡ በትግራይ ክልል 95ሺ የሚደርሱ ነጋዴዎች ግብር መክፈል መጀመራቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል 95ሺ ገደማ ነጋዴዎች ካለፈው አመት ጀምሮ ግብር መክፈል መጀመራቸውን የክልሉ ገቢዎች እና ልማት ባለሥልጣን አስታወቀ።

ካለፈው በጀት ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በክልሉ ግብር እየተሰበሰበ መሆኑን እና ከግብር የሚገኝ ገቢ የተሳለጠ እንዲሆን በጥናት የተደገፈ አሠራርም እየተዘረጋ እንደሚገኝ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወልደገብርኤል አፅብሃ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ክልሉ በጦርነት ውስጥ በመቆየቱ የተነሳ ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ በርካታ ሰነዶች እንደ አዲስ እያደራጀን ነው ሲሉ ሃላፊው መናገራቸውን ያስታወቀው ዘገባው 95ሺ ገደማ ከሚሆኑ ነጋዴዎች ግብር መሰብሰብ እንደተቻለ መግለጻቸውን አካቷል፡፡

የትግራይ ክልል 25 ሺህ ለሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ግብር ከፋይ ማህበረሰብ የ2013/14 ክፍያ ምህረት መደረጉን ሃላፊው መግለጻቸውን እና ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚደርስ መናገራቸውን ጠቁሟል።

ምህረት የተደረገውም በጦርነቱ ምክንያት የነበረው ጫና ለማቅለልና በፍጥነት ወደ ሥራ መግባት እንዲቻል ነው ሲሉ አብራርተዋል ያለው ዘገባው ጦርነቱ በመሠረተ ልማት እና ኢኮኖሚ ላይ የፈጠረው ጫና ቢኖርም ሰላም ከተፈጠረ በኋላ ጥሩ ጅማሮ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ስራው የበለጠ እንዲሳካ የቁሳቁስ እና መሰል ክፍተቶች እዲሟሉ እየተደረገ እንደሚገኝ መግለጻቸውን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ዕቅድ አውጥቶ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ሥራ መግባቱን የጠቀሱት ኃላፊው ወደ ሥራ የገባነው እጃችን ላይ ባለው ከውድመት የተረፈ ሀብትና የሰው ኃይል ነው ሲሉ መጥቀሳቸውንም አካቷል።

ተበታትኖ የቆየውን የሰው ኃይል በማሰባሰብ ወደ ምድብ ሥራው እንዲሰማራ መደረጉን ሃላፊው መናገራቸውን አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button