ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና የምትሰጠው ሁኔታውን በጥልቀት ካጤነች በኋላ መሆኑን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24/2016 .ም፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና የምትሰጠው ሁኔታውን በጥልቀት ካጤነች በኋላ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረው የመግባቢያ ሰነድ ሁሉን አቀፍ የትብብርና አጋርነት ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቆመው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሰነዱ ታሪካዊ የሚባሉ ጥያቄዎችን በሚመልስ፣ ዝርዝር ፣ግልጽና ስትራቴጂክ አጋርነትን በዘላቂነት ለመገንባት የሚያስችል ነው ሲል ገልጿል።

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ ዘላቂና አስተማማኝ የባሕር ኃይል ቤዝና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሊዝ የምታ7ኝበትን ዕድል የሚያስገኝላት መሆኑን የጠቆመው መግለጫው ሶማሌላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት እንደሚያስችል አስታውቋል።

በተጨማሪም ሶማሊላንድ ማንም አገር እየፈለገ ሊከውናቸው የማይችሉ ጥያቄዎቻቸውን የሚመልስ እንዲሁም ከማንም ሀገር ሊያገኙት የማይችሉትን እገዛና ሽርክና ያጎናጽፋቾዋል ሲል ገልጿል።

ከዚህ ቀደም በርበራ ላይ ለኢትዮጵያ የ19 በቶ ድርሻ እንዲኖራት ይፈቀድ የነበረ የግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ እንደነበርም ያወሳው መግለጫው በአሁኑ ወቅት ሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ሂደት እተከተሉ ቢሆንም የተሰማ ኮሽታም ሆነ ቅሬታ አልነበረም ሲል በስምምነቱ ዙሪያ የሚሱ ተቃውሞዎችን ተችቷል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ቁጭትና ቁዘማ ለማከም የሚያስችል አጋጣሚን የፈጠረ ነው ሲል የገለጸው መግለጫው በመሆኑም ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስደስት ታሪካዊ ክስተት ነው ብሎታል። ሁሉም ኢትጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም የቀጣናው ሰላም የሚገዳቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ሁሉ ሊደሰቱ ይገባል ብሏል።

በዚህ ስምምነት ሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም ሲል የገለጸው መግለጫው የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም ሲል አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button