ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመከባበር ላይ ተመስርተው “የተፈጠረውን ውጥረት” እንዲያረግቡት ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም፡- የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃመት በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው ስምምነት ተከትሎ “የተፈጠረውን ውጥረት በቅርበት እየተከታተሉት” መሆኑን አስታውቀው “ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመከባበር ላይ ተመስርተው ውጥረቱን እንዲያረግቡት” ጥሪ አቅርበዋል

ሊቀመንበሩ አክለውም “ሁለቱም ሀገራት በአመታት የገነቡትን መልካም ግንኙነት ሊያበላሽ ከሚችል ማናቸውም እንቅስቃሴ ከማድረግ” እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

“የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መንግስታትን ጨምሮ ሁሉንም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አንድነትን እና የግዛት ሉአላዊነትን ማክበር በጣም አስፈላጊ ነው” ሲሉ አሳስበዋል።

ሊቀመንበሩ በተጨማሪም በመግለጫቸው በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምን፣ ደህንነትን እና መረጋጋትን ለማስፈን እና ለማጠናከር የመልካም ጉርብትና ደንቦችን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

ሁለቱ ወንድማማች አገሮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት እጅግ ገንቢ፣ ሰላማዊ እና ትብብርን በተሞላበት መንገድ ለመፍታት እና በአካባቢው ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን ትብብራቸውን ለማጎልበት ሳይዘገዩ ወደ ተግባር እንዲገቡ ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው ጠይቀዋል።

ለዚህም ህብረቱ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባህር በር ለመስጠት እና በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት በጠ/ሚኒስትር አቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መካከል በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰንድ መፈረሙ ይታወቃል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይ የአዉሮፓ ህብረት ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ ሉዓላዊነት ሊከበር ይገባል ሲል በማሳሰብ የሶማሊያ የድንበር ወሰን፣ አንድነቷ እና የሀገሪቱ ክብር ሊጠበቅ ይገባል ማለቱ ይታወሳል፤ ሁሉም አካላት ወደ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት እንዲመጡ አሳስቧል።

ኢጋድ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ሁኔታ በጥንቃቄ እየተከታተለው እንደሚገኝ በመግለጽ በቀጠናው ሰላም ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ እንደሚገነዘብ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።  ኢጋድ በመግለጫው  ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስለተፈራረሙት መግባቢያ ሰነዱ ያለው ነገር የለም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button