ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 67 ቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት መስማማቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ 67 ቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር መስማማቱን አስታወቀ። 11 ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን፣ 20 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ለቦይንግ ኩባንያ ትእዛዝ ማቅረቡን በይፋ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በቀጥታ የግዢ ስምምነት ከፈጸመባቸው 31 አውሮፕላኖቹ በተጨማሪ እንደሁኔታው በቀጣይ 15 ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን እና 21 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለመገዛት ስምምነት ላይ መድረሱን አመላክቷል።

በአጠቃላይ አየር መንገዱ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ለመግዛት የተስማማው የአውሮፕላን ብዛት 67 መሆኑን በመግለጫው ጠቁሟል።

መግለጫው በማያያዝም በዱባይ አለም አቀፉ የአየር ትርኢት ላይ የተፈረመው ስምምነት በአየር መንገዱ ታሪክ ትልቁ ግዢ የተፈጸመበት መሆኑን ጠቁሟል።

አየር መንገዳችን ከቦይንግ ኩባንያ 31 እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን እና እንደ ሁኔታው ደግሞ ተጨማሪ 36 ተጨማሪ ጀቶችን ለመግዛት ስምምነት ላይ በመድረሳችን ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማን መግለጽ እንወዳለን ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

አውሮፕላኖቹን ለመግዛት የተደረሰው ስምምነት በ2035 ልናሳካው ያቀድነውን ራዕይ እውን ለማድረግ ያግዘናል፣ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ያለንን የቆየ ግንኙነት ያጠናክርልናል ብለዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button