ዜናቢዝነስ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በቻይና የፋይናንስ ተቋማት የተያዘባትን አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊየን ዶላር ብድር ለማስለቀቅ እየተወያየች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም፡- በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ በቻይና ባደረገው ጉብኝት ከሀገሪቱ ኤግዚም ባንክ (Export-Import Bank) ሊቀመንበር እና ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ማካሄዱን ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ገልጿል።

ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በመጓዝ በቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ በመሳተፍ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ውስጥ የተካተተው እና በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው የፋይናንስ ልዑክ ከቻይና ኤግዚም ባንክ ሃላፊዎች ጋር ያደረገው ውይይት ዋነኛ አላማ ኢትዮጵያ በቻይና የተያዘባትን አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊየን ዶላር ብድር ለማስለቀቅ መሆኑ ተመላክቷል።

ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ሊቀመንበር ከሚስተር ውፍሊን እና ከባንኩ ሀላፊ ዋኑ ጋር በተደረገ የጋራ ስብሰባ ላለፋት ዓመታት በባንኩ የተያዘው የብድር ክፍያ ለፕሮጀክቶች በሚለቀቅበትና የብድር ክፍያ ሽግሸግ በሚደረግበት ጉዳይ ላይ መሆኑን የጠቆመው የሚኒስቴሩ መረጃ ከባንኩ የስራ ኃላፊዎች አበረታች ምላሽ ማግኘቱን አስታውቋል።

በአሁኑ ሰአት የቻይና መንግስት የኢትዮጵያን ብድር ሁኔታ አስመልክቶ ውሳኔ እስኪያሳልፍ ድረስ በሚል ከቻይና የፋይናንስ ተቋማት ማለትም ከቻይና ኤግዚም ባንክ፣ ከቻይና ልማት ባንክ እና ከቻይና የኢንደስትሪ እና ኮንስትራክሽን ባንክ ያልተለቀቀ ከ758 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ብድር እንደሚገኝ ተጠቁሟል። በተጨማሪም የቻይና መንግስት እንዳይለቀቅ ያደረገው ሌላ 576 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚገኝ ተገልጿል።

ብድሩ የሚለቀቀው የቻይና መንግስት የኢትዮጵያን የብድር ሁኔታ ገምግሞ ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ መሆኑም ተገልጿል።

የብድሩ መዘግየት በሀገሪቱ በሚገነቡ እና በመገንባት ላይ ባሉ መሰረተ ልማቶች ላይ መጓተት ማስከተሉን እና በተለይም በስምንት መሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተጠቁሟል። ሚኒስቴሩ በፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባቀረበው መረጃ ልዑኩ ከቻይና ልማት ባንክ ዋና ሃለፊ ሚስተር ዋንግ ዎልዶንግ፣ ከምክትሎቻቸው እና ከተለያዩ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የብድር ክፍያ ማራዘሚያ ድርድር በቶሎ በሚቋጭበትን እና ባንኩ በቀጣዩ የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል ብሏል፡፡

ከዚህም ሌላ ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ መዋዕለነዋያቸውን ካፈሰሱና ወደፊት በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ስራዎች መሳተፍ ከሚፈልጉ ኩባንያዎች የስራ ኃላፊዎች ጋር የተናጥል ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኢትዮጵያ ልማት ለሚሳተፋ የቻይና ድርጅቶች የሚደረገው የመንግስት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፋይናንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በውይይቱ ለተሳተፋ እንዳረጋገጡላቸው በመረጃው ተጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button