ጤናዋና ትረካ
በመታየት ላይ ያለ

ትረካ፡ የአሜሪካ ቶፕ ታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊው የ14 አመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሄመን በቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም:- የ14 አመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሄመን በቀለ የአሜሪካ ቶፕ ታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸነፊ ሆኗል። ታዳጊው ሄመን አሸናፊ ለመሆን ያበቃው የቆዳ ካንሰርን የሚከለክል ሳሙና መስራቱ ነው። 

ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ሰዓታት ለፀሀይ በሚያጋልጥ ሁኔታ ላይ ሆነው የሚሰሩ ሰዎች ማየቱ ከትውስታው ያልጠፋው ሄመን ይህን ሳሙና ለመስራት እንዳነሳሳው ይናገራል። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ለቆዳ ካንሰር ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን እና ለህክምና 40 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልጋቸው በመረዳት መፍትሄ ማፈላለግ ይጀምራል።

“ሰዎች ከህክምና እና ለቤተሰባቸው ምግብ በጠረጴዛ ላይ በማኖር መካከል መምረጥ እንዳለባቸው በመንገንዘቤ በጣም አዘንኩ” ሲል የሚናገረው ይህ ታዳጊ ሳይንቲስት ይህን ለመቅረፍ ስለ ቆዳ ካንሰር ጥናት በመስራት ጀመረ። 

በዚህም ሂደት ስለ ዴንድሪቲክ ህዋሶች ማወቅ ቻለ። ይህም በሽታ የመከላከል አቅምን በማሳደግ ቆዳን ለመጠበቅ እንደሚረዳ በመረዳት የቆዳ ካንሰርን መከላከል የሚችል ትክክለኛ ውህደቶችን ለማግኘት ወራትን ያስቆጠረ ምርምር አድርጎ በመጨረሻም የኮከነት ዘይት፣ ካኪሎን የተባለ የቆዳ ክሬም እና ተፈጥሯዊ የሺያ ተክል ፍሬን በመጠቀም የቆዳ ካንሰርን መከለል የሚችል ሳሙና መስራት ቻለ።

የሄመን ሳሙና ለቆዳ ካንሰር የሚወጣውን 40 ሺህ ዶላር ወጪ በ 0.50 ዶላር መካለክ ያስችላል ነው የተባለው።

በዚህም ስራው የዘንድሮውን የአሜሪካስ ቶፕ ያንግ ሳይንቲስት “America’s Top Young Scientist” የተሰኘውን ውድድር ማሸነፍ የቻለው ሄመን በቀለ 25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተበርክቶለታል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄመን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውን ማህበረሰብ የቆዳ ካንሰርን መከላከል የሚችለውን ሳሙና ለማከፋፋል ይረዳው ዘንድ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት መመስረቅ የወደፊት እቅዱ መሆኑ ፈየርፋክስ ካውንቲ የተባለው ትምህርት ቤቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷልአስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button