ዜናቢዝነስ

ዜና፡ መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው አሚአ ፓወር 300 ሜጋዋት የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መንግስት ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ኩባንያ ከሆነው አሚአ ፓወር ጋር በሶማሌ ክልል 300 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ከንፋስ ሀይል ለማመንጨት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ተገለጸ።

በሶማሌ ክልል የሚገነባውን የንፋስ ሀይል ማመንጫውን ለመገንባት 600 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደሚጠይቅ ሮይተርስ የዜና ወኪል የገንዘብ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ፕሮጀክቱ በሚገነባበት ወቅት እና ከተገነባም በኋላ ለሁለት ሺ ሰው የስራ እድል ይፈጥራል መባሉን ዘገባው አመላክቷል።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ግንባታውን አስመልክቶ ባቀረቡት ዘገባ በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሶስት አመታት ጥናት ቀድሞ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button