ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ ጋዜጠኞችን ጨምሮ የሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 23 ተከሳሾች ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/2016 ዓ.ም፡- አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 23 ተከሰሳሾች ካቀረቧቸው አራት የክስ መቃወሚያዎች ውስጥ ሦስቱ በፍርድ ቤት ውድቅ ሲደረጉ፣ ተከሳሾች በዝርዝር የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ ደግሞ ተቀባይነት ማግኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ተከሳሾቹን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው ትላንት ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ በሕገ መንግስት ጉዳዮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመለከተው ችሎት መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።

ችሎቱ ለትላንት ህዳር 12 የተቀጠረው የተከሳሽ ጠበቆች በጽሁፍ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ እና የዐቃቤ ሕግን መልስ መርምሮ ብይን ለመስጠት እንደነበር አስታውቋል።

ጠበቆች በ10 ገጾች ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበው ክስ “የፖለቲካ አጀንዳ የያዘ” መሆኑን በመጥቀስ ክሱ ወድቅ እንዲደረግላቸው የጠየቁ ቢሆንም የተከሳሽ ጠበቆች ክሱን የተቃወሙት አራት ጉዳዮችን በማንሳት መሆኑን ከተከሳሾቹ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ እንደነገሩት ቢቢሲ በዘገባው አካቷል።

ጠበቆቹ በክስ መቃወሚያቸው ያነሱት ቀዳሚው ነገር “አንደኛ የተከሰስንበት ጉዳይ የሽብርን ሕግ የሚያሟላ አይደለም በአገራችን ሕግ መሠረት ሽብር ተብሎ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ አይደለም” የሚል መሆኑን ጠበቃ ሄኖከ ገልጸዋል።

ቢቢሲ በተመለከተው የክስ መቃወሚያ ላይ ጠበቆች በዐቃቤ ሕግ ክስ ላይ፤ “የፖለቲካ እና ርዕዮተ ዓለም ግባቸውን በኃይል ለመጫን [ተንቀሳቅሰዋል]” በሚል የቀረበባቸውን ውንጅላ ተቃውመዋል ብሏል።

ይህ የዐቃቤ ሕግ ክስ በጠበቆች ተቃውሞ የደረሰበት፤ “የትኛውን ፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ለመቀየር እንደታሰበ በክሱ ላይ በግለጽ መጠቀስ ይኖርበታል” በሚል መሆኑን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ለመቃወሚያው በሰጠው የጽሁፍ ምላሽ ተከሳሾች ያቀረቧቸው ክርክሮች “የተከሰሱበትን ሕግ እና የቀረበባቸውን ክስ በአግባቡ ካለመረዳት የመነጨ ነው” ማለቱን አካቷል።

በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ያገኘው እና ሌላኛው የክስ መቃወሚያ ዝርዝር የፍሬ ነገሮች ጉዳይን የተመለከተ መሆኑን ያስተወቀው ዘገባው ጠበቆች በክስ መቃወሚያቸው ላይ “ወንጀሉ የተፈጸመበት ጊዜ እና ስፍራ፣ የተበደለው ሰው ስም፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ንብረት በክሱ ላይ በግልጽ መቅረብ አለበት” ማለታቸውነ አመላክቷል።

የችሎት ውሎ ከመጠናቀቁ በፊት በቀጣይ ቀጠሮ “ዐቃቤ ሕግ የተጠቀሱትን ፍሬ ነገሮች በክሱ ላይ አጠቃልሎ እና አሻሽሎ እንዲቀርብ” ትዕዛዝ መሰጠቱን ጠበቃው እንደነገሩት ቢቢሲ በዘገባው አስታውቋል።

በዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ ስም በሚጠራው መዝገብ ላይ ክስ የተመሰረተባቸው 51 ግለሰቦች ቢሆኑም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ግን 23ቱ ብቻ መሆናቸውንም ጠቁሟል።

በቃሊቲ እና በቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙት 23ቱም ተከሳሾች ትላንት ህዳር 12 ቀን በችሎት በአካል ተገኝተው ጉዳያቸውን መከታተላቸውን እና ከ23 ተከሳሾች መካከል የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ መስከረም አበራ፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ዳዊት በጋሻው እና ገነት አስማማው እንደሚገኙበት ዘገባው አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button