ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በክልሉ ለሚገነባው ከ600 በላይ የፖሊስ ጽ/ቤቶች ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ ከህዝቡ ማሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17/ 2016 ዓ/ም፡ በሲዳማ ክልል በህብረተሰብ ተሳትፎ ለሚገነቡ 640 የፖሊስ መቆጣጠሪያ እና የስምሪት ቀጠና ጽ/ቤቶች ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ ከህዝቡ ማሰብሰቡን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቁ። 

አቶ አለማየሁ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት፣ በመላው የክልሉ አከባቢዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ የፖሊስ ፅ/ቤቶችን መገንባት ያስፈለገው በመንግስት አቅም ማከናወን ባለመቻሉ እና በህብረተሰቡ እና በፖሊስ መካከል አብሮነትንና ግንኙነት ለማጠናከር ይርዳል በሚል ዕሳቤ ነው።

የጸጥታ ተቋማት ቋሚ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል ያሉት ሃላፊው ፅ/ቤቶቹ ሰራቸውን የሚያከናውኑት በኪራይ ቤቶች በመሆኑ ፖሊስ በየጊዜው አድራሻውን ለመቀየር መገደዱን እና ይህም ህብረሰተቡ ላይ ተጽዕኖ ማድረሱን ገልጸዋል። 

አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ “ለፖሊስ ማዕከላት የሚሰጠው በጀት በቤት ክራይ፣ በፓትሮል ራውንድ ነዳጅ ብቻ እያለቀ ተቸግረናል የሚሉ ድምፆች ከመቀነስ ባለፈ የቤት ባለቤቶች ቤታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ለፖሊስ ፅ/ቤት ቤት ለማከራየት ፍቃደኛ በለመሆን በተቋሙ ላይ የሚደርሰውን እንግልትና ችግር ይቀርፋል ብለን እናምናለን” ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ በኪራይ ቤቶች ስራቸውን እያከናወኑ ያሉ የፖሊስ ፅ/ቤቶች ላይ በየጊዜው የሚስተዋለውን የክፍያ ጭማሪ እና አላስፈላጊ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ ያስቆማል ተብሏል። ከሺህም ባሻገ ለህዝቡ የፖሊስ አቀፉን ስራ ለ24 ሰዓት በአቅራቢያ እንዲያገኝ የሚያስችል መኖኑን ሃላፊው ተናግረዋል።

በ90 ቀናት ውስጥ በቀበሌ ማዕከል ለመገንባት ከታቀዱት 640 የፖሊስ ጽ/ ቤቶች ውስጥ 390 ግንባታቸው መጠናቀቃቸውን አቶ አለማየሁ ገልጸዋል። የክልሉ መዲና በሆነችው የሃዋሳ ከተማ ብቻ ከ40 በላይ የፖሊስ ፅ/ቤቶች ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆን በዚህም በከተማዋ የሚገነቡ ሁሉም ፅ/ቤቶች በቴክኖሎጂ የበለፀጉ እንደሆነም ሃላፊው ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ከሚገነቡት ጽ/ቤቶች ውስጥ 40 የሚሆኑት አያንዳንዳቸው ከ10 እስክ 15 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረገባቸው መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።  

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሁሉንም ግንባታዎች በቀሩት 30 ቀናት ውስጥ ለማጠናቅቅ እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊው “ሀብረተሰቡ እና አምራሩ እያደረገ ያለው ንቅናቄ በታሪክ ታዮቶ የመየታወቅ ነው” ሲሉ አድንቀዋል። 

በሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና በሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ከህዝቡ ጋር በመሆን በመላው የክልሉ አከባቢዎች የፖሊስ ፅ/ቤቶች 800 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ መሆኑን ገልጸዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button