ዜናቢዝነስ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ አለም አቀፍ ሰራተኞቹን በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ እንደሆነ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10/2016 .ም፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ አለም አቀፍ ሰራተኞቹን በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ እንደሆኑ ሮይተርስ የዜና ወኪል ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአንድ ወር በፊት በሁለት አለም አቀፍ ሰራተኞቹ የዲፕሎማሲያዊ ፕሮቶኮላቸው በመገፈፉ እና በፀጥታ አካላት ድብደባ መፈፀሙን ተከትሎ መሆኑን አመላክቷል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአዲስ አበባ በሚገኘው ቢሮው ባልደረባ የሆኑ ሁለት ሰራተኞቹ ላይ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ከህግ አግባብ ውጭ አስረዋቸው እንደነበር፣ ድብደባ እንደፈጸሙባቸው እና የዲፕሎማቲክ መብት ጥሰት እንደደረሱባቸው ማስታወቁን አውስቷል።

ባንኩ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ደብዳቤ እንደገለጸው የተፈጸመባቸው እስር ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ መብት ጥሰት ነው ሲል ተችቶ ስለሁኔታው ለኢትዮጵያ መንግስት ማስታወቁን እና ተቀባይነት ማግኘቱን፣ ነገር ግን ስለ ተፈጸመባቸው ድብደባም ሆነ ስለ አመራሮቹ ማንነት አለመግለጹን መዘገባችን ይታወሳል።

በባንኩ ፕሬዝዳንት ተፈርሞ የወጣ እና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ደብዳቤ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ የሚገኘው ቢሮው ግን በሀገር ውስጥ ሰራተኞቹ አገልግሎት መስጠቱን እንደሚቀጥል ተጠቁሟል። ባንኩ አለም አቀፍ ሰራተኞቹን ከአዲስ አበባ ለማስወጣት የወሰነው ውሳኔ የሀገር ውስጥ ሰራተኞቹ ላይ ምንም ተጽእኖ አይኖረውም ሲል ገልጿል።

ባንኩ ከጉዳዩ ጋር በተያየዘ ከጠ/ሚኒስትሩ እና ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር መነጋገሩን ጠቁሞ በተጨማሪም ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራ ቡድን በጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መምከሩን አስታውቋል።

ቡድኑ ባደረገው ምርመራ ጉዳዩ የባንኩን ፍላጎት በሚያረካ መልኩ እልባት የተሰጠው ባለመሆኑ እና አለም አቀፍ ሰራተኞቹን ደህንነት በተጠበቀ መልኩ ያለሰቀቀን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው ለመስራት የሚያስችላቸው መተማመን መፍጠር ባለመቻሉ ውሳኔው ላይ መድረሱን አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ሁኔታ ለባንኩ ባለማሳወቁ የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት በጻፉት ደብዳቤ  ጉዳዩን አስመልክቶ ለባንኩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ ማሳወቃቸውን ጠቁመው ቀጣይ እርምጃዎች ላይም ማብራሪያ ማቅረባቸውነ አመላክተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button