ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያ በአግባቡ እየተሰበሰበ እንዳልሆነ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20/2016 ዓ.ም፡- በባለድርሻ አካላት የእርስ በርስ መናበብና መቀናጀት ከፍተት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያ በአግባቡ እየተሰበሰበ እንዳልሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የተማሪዎችን የወጪ መጋራት ክፍያን በወቅቱ ተከታትለው የሚያስፈጽሙ ተቋማት ቢኖሩም በርካታ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተዘረጋው የአሠራር ሥርዓት መሠረት ክፍያውን ተከታትለው በማስፈጸም ረገድ ክፍተት እንደሚታይባቸው በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደርና መሠረተ-ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብረሃ ገልጸዋል።

በመሆኑም የመንግሥት ገንዘብ በአግባቡ ተሰብስቦ ለተመሳሳይ ዓላማ ጥቅም ላይ እንዲውል ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ አቶ አብዶ ናስር በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያ መከፈል በሚገባው ወቅት አለመከፈሉ የመንግስትን ተጨማሪ የኢንቨስትመንት አቅም የሚገድብ መሆኑን ጠቅሰው ተማሪዎችም የተጋሩትን ወጪ በሚጠበቅባቸው ወቅት ካልከፈሉ ለተጨማሪ የወለድ ክፍያም ሆነ ተሰብሳቢ እዳ የሚጋለጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ አብዶ አክለውም ይህንን ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ ትምህርት ሚኒስቴር በአሰራር፣ በመረጃ ጥራትና በክትትል ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላትም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በተገኙበት በከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ወጪ መጋራት ዙሪያ  ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መካሄዱን ከትምህርት ሚኒስቴር ይፋዊ የፌስቡክ ማህበራዊ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button