ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የዓለም ሥራ ድርጅት ያጸደቃቸውና ኢትዮጵያ ያላካተተቻቸውን ስምምነቶችን እንድትፈርም የሚጠይቅ አጋርነት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13/2016 ዓ.ም፡- በዓለም ሥራ ድርጅት ድንጋጌዎች ውስጥ የተካተቱ እና ኢትዮጵያ እስካሁን ያልፈረመቻቸው ስምምነት ቁጥሮች 189፣190፣97 እና 143 ፈርማ የሕጎቿ አካል እንድታደርጋቸው ለመጠየቅ የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ እየተካሄደ ነው፡፡

የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተከናወነ መርሀግብር ዘመቻው መጀመሩ ከኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

እነዚህ የቤት ሠራተኞች መደራጀትን፣ በሥራ ቦታ የሚደርስ ጥቃትና ትንኮሳን የሚመለከተውን እና ፍልሰተኛ ሠራተኞችን የሚመለከተውን የዓለም ሥራ ድርጅት ስምምነቶች ኢትዮጵያ እስካሁን ፈርማ የሕጓ አካል አለማድረጓ በሠራተኞች ሰብዓዊና የሠራተኛ መብት መከበር ላይ እንቅፋት እየሆነ መሆኑን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ የአጋርነት ጥሪ ነው ተብሏል።

የነዚህ ሕጎች የኢትዮጵያ ሕግ አካል መሆን የሠራተኞችን ሰብዓዊና የሠራተኞች መብት ከማስከበራቸው ባሻገር በአገራቸው የሚያከናውኑዋቸውን ሁለንተናዊ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ያስችላቸዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በዘመቻው ማስጀመሪያ ላይ መናገራቸውን መረጃው ያሳያል።

እነዚህ ስምምነቶች የኢትዮጵያ ሕግ አካል መሆናቸው ለተገፉት ሁሉ ድምጽ የሚሆን እና ፋይዳውም ለአገር መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቤት ሠራተኞች በማኅበር መደራጀታቸው እያከናወኑ ያሉትን ሁሉንም የሚያግዝ ተግባር ይበልጥ በተቀናጀና በዘመነ መልኩ ለማከናወን እንዲችሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ራኬብ መሰለ ባሰሙት የአጋርነት መልዕክት በተለይ ፍልሰተኛ ሠራተኞችን ጉዳይ በተመለከተ መብት ማስከበርን ከሥራ ልምዳቸው ተነስተው የተመለከተው የስምምነት ቁጥር 97 መፈረም ምን ያክል ለሥራ ከአገራቸው ውጪ በመሄድ ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button