ዜናማህበራዊ ጉዳይቢዝነስ

ዜና፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5/2016 .ም፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ማስፈጸሚያ ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ማጽደቁ ተለጸ።

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በምክር ቤቱ የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዕንቁ ዮሐንስና የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በጋራ የክልሉን መንግስት የስራ ዘመኑ በጀት ለምክር ቤቱ አቅርበው ማስጸደቃቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውቋል፡፡

በጀቱ በክልሉ በሚገኙ 12 ዞኖች ለመንግስት የመደበኛና ካፒታል ሥራዎች የሚውል መሆኑን የጠቆመው ዘገባው በዚህም ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች መደበኛና ካፒታል ወጪ፣ ለዞኖች ጥቅል በጀት፣ ለክልላዊ ፕሮግራሞች፣ ለዘላቂ ልማት ግቦችና ለመጠባበቂያ አጠቃላይ ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በምክር ቤቱ ማጽደቁን አመላክቷል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button