ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የ‘ቢዝነስ አውትሶርሲንግ’ ዘርፍ ለኢትዮጵያ በአመት 50 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል፣ ለ15 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12/2016 .ም፡ ሥራን ለሶስተኛ ወገን በመስጠት በሚከናወነው አውት ሶርሲንግ ዘርፉ በውጭ ሀገራት በኢንተርኔት አማራጭ በተሠሩ ሥራዎች በዓመት 50 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። እስካሁን በዘርፉ ለ15 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠሩንም አመላክተዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አውት ሶርስ ማህበር ጋር በመተባበር በዘርፉ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግና የሥራ እድልን ለመፍጠር መንግሥት ተኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ሲሉ ሚኒስትሯ መናገራቸውንም አስታውቋል።

በቴሌኮም ዘርፍና በተለያዩ የኢንተርኔት አማራጮች በሚከናወኑ ሥራዎች አማካኝነት የአውትሶርሲንግ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል ያለው ዘገባው ቢዝነስ አውትሶርሲንግ ሥራ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቲጂ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ ዜጎች እራሳቸውን ብቁ አድርገው እንዲገኙ ለማድረግ ለዘርፉ የሚመጥን ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ በኮሌጆች በኩል ሥልጠና ለመስጠት ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው ሲሉ አስረድተዋል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት የሰጠ ሲሆን አሁን በተከለሰው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ውስጥም የዲጂታል ቢዝነስ አውትሶርሲንግ የሥራ ዘርፍ ልዩ ማበረታቻ ከሚሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ እንዲካተት መደረጉን ተናግረዋል።

የአውት ሶርሲንግ ኢንዱስትሪ የሥራ እድል ከመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ከማሳደግ፣ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የእውቀት ሽግግርን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ የኢትዮጵያ አውትሶርስ ማህበር ፕሬዚዳንት ወንድወሰን ዘውዱ መግለጻቸውን ያመላከተው ዘገባው በዲጂታሉ ዘርፍ ሥራ በመፍጠር ከዘርፉ ሀገራችንን ተጠቃሚ ለማድረግ እስካሁን የተደረጉት ጥረቶች እንዳሉ በማንሳት በቀጣይም ዓለምአቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ያስገቡ ማበረታቻዎች እና የቅንጅት ሥራዎች ያስፈልጋሉ ማለታቸውን አካቷል።

በዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በ 2023 ዓ.ም ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማድረስና በዘርፉ የሚሠሩ ዜጎችን ቁጥር 500 ሺህ ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል ማለታቸውንም አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button