ፖለቲካትንታኔቢዝነስ
በመታየት ላይ ያለ

ትንታኔ፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሄዱ ያሉ ግጭቶች እና አለመርጋጋቶች የቱሪዝም ዘርፉ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅነዋል

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3/2016 ዓ/ም፡ ኢትዮጵያ የበረካታ ቱሪስት መስህቦች ባለቤት ከሆኑ አገራት መካክል አንዷ ናት። በተያዘው አመት እንኳ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የትምህርት ተቋም (ዩኔስኮ) በሶስት ዘርፎች ተጨማሪ ቅርሶችን መዝግቧል። ባሳለፈነው ሳምንት የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር የአለም የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ በመሆን የተመዘገብ ሲሆን ቀድም በሎም የባሌ ተራሮዎች ብሔራዊ ፓርክ በተባባሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና እና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በአለም ቅርስነት ተመዘግቧል፡፡ በተጨማሪም የሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና የተሰጠው ሲሆን የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውም በዚሁ አመት ነው።  

ይህም ኢትዮጵያ ቀድሞውኑ ከነበራት የቱሪስት መዳረሻዎች እና በመንግስት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ጋር ተደምሮ አለም አቀፍ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ረገድ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው። ነገር ግን በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶች የቱሪዝም ዘርፉ ላይ ፈተና ደቅነዋል። 

በአለም አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ እነቅስቃሴን ያስቆመው የኮቪድ ወረርሽን ሰጋትነት ማብቃቱን ተከትሎ የበርካታ አገራት የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም በመነቃቅት ላይ ቢገኝም በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ያሉት ግጭቶች ግን  የዘሩፉን አንቅሰቃሴ እያዳከሙ መሆኑን ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ የዘረፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል ተጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋው እና ለሁለት አመታት የዘለቀው አውዳሚ ጦርነት የክልሎቹን የቱሪዝም እንቅስቃሴን ሙሉ ለሙሉ ገድቦት ቆይቷል። ምንም እንኳ በፕሪቶሪያው ስምምነት ጦርንቱ ቢቋጭም  ከትግራይ ክልል ቱሪዝም ዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱን ከክልሉ የሚሰጡ መግለጫዎች አመላክተዋል።

ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት የአለም ቱሪዝም ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ሪፖረት የትግራይ ጦረነት በስምምነት ማብቃትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቱሪዝም 28 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲል ገልጿል። የቱሪዝም ሚኒስቴርም ስኔ ወር ላይ ባወጣው መግለጫ የሰላም ስምምነቱ ከተደረሰ በኋላ ባሉት ዘጠኝ ውራት ውስጥ ከ700 ሺህ በላይ ጎብኝዎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል ብሏል። 

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሃሳባቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ያጋሩ የዘረፉ ባለሙያውች በዚህ አይስማሙም። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እያተካሄዱ ባሉት ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ምክንያት ለጉብኝት ወደ አገር ውስጥ የሚመጡ ጎብኝዎች እጅግ አንስተኛ መሆኑን እና ዘርፉም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። በረካታ አጋራት ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የጉዞ ክልከላ በማደረጋቸው አሁን ላይ በአዲስ አበባ ለሚካሄዱ ስብሰባዎች  የሚመጡ እንግዶች ካልሆነ በስተቀር በመደረሻዎች ለሚደረግ ጉብኝት የሚመጣ ቱሪስት ቁጥር እዚህ ግባ የማይባል መሆንን ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል።

መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሶ ለማደራጅት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በአማራ ክልል በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል የተቀሰቀስው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል። ይህም የሰዎች ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እያደረስ ይገኛል። በክልሉ እየተካሄድ ባለው ግጭት መንገዶች በመዘጋታቸው በቱሪስቶች ወደ  ክልሉ መዳረሻዎች የሚደረጉ እንቀሰቃሴን ገትቷል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በቱሪስት መስህብነቱ የበረካታ ጎብኚውችን ልብ የመሳብ አቅም ያለው አማራ ክልል በግጭት ምክንያት በክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትጽዕኖ እያደረሰ መሆኑን በክልሉ በአስጎብኚነት ስራ ላይ ተሰማረቶ የሚገኝ ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው አስጎብኚው “በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት እና የእንቀሰቃሴ ገደብ በመኖሩ ምክንያት ወደ ከልሉ የሚመጡ ጎብኚዎች የሉም” ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። በዚህም የተነሳ በዘረፉ ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ ተጽዕኖ እየደረስ መሆኑን አስጎብኚው ጠቅሷል። “ ከጦርነቱ በኋላ ትንሽ መነቃቃት ነበር አሁን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የቱሪዝም ዘርፉ ቆሟል፤ ሰላም እስኪውርድ ቁጭ ብለን እየተበቀን ነው” ሲል በክልሉ ያለውን የቱሪዘም ዘረፉን መዳከም ገልጿል።

በክልሉ የጎንደር የሚገኙ ታሪካዊ ቅረሶች፣ የሰሜን ተራሮች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተ ክርስቲያናት እንዲሁም ባህርዳር የጉብኝት መዳረሻዎች መሆናቸውን የጠቀሰው አስጎብኚው “በክልሉ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ስጋት በመኖሩ ከቱሪስቶች ጋር የሚደረጉ ጉዞዎችን እያካሄድን አይደለም” ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ አስረደቷል። 

ግጭቶች እና አለመርጋጋቶች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ በዘረፉ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በልተው ማደር የማይቸሉበት ደረጃ ላይ መድረሳችው አይቀሬ መሆኑንም ነው የገለጸው። 

ናሆም አድማሱ ታላቂቷ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር አባል እና ፕሌዠር ኢትዮጵያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ድርጅት ባለቤት ነው። ናሆም ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረገው ቆይታ፣ የቱሪዝም ዘርፉ ከሰላም እና መረጋጋት ጋር አብሮ የሚጓዝ መሆኑን ገልጾ በየትኛውም አካባቢ አንስተኛ አለመረጋጋት እንኳ ካለ እንቅስቃሴዎችን ያስትጓጉላሉ ብሏል። ይህም ጎብኚዎችን እንደሚያሳጣ ገልጿል።  እንቀስቃሴዎች ሲስተጓጎሉ በቱሪዝም ሰንሰለት ውስጥ ያሉ አካላት በሙሉ ተጎጂ ይሆናሉ ሲል የገለጸው ናሆም ከአየር መንገድ ጀምሮ እስክ በመዳረሻ አካባቢ ያሉ ሆቴሎች፣ ሬስቱራንቶች፣ አስጎብኚዎች፣ አገልግሎች ሰጭ አካላት ሁሉ ገቢ የሚያሳጣ መሆኑንም አስረደቷል። 

እንዳንዱ ከዘርፉ ተጠቃሚውች ስር ያሉ ቤተሰቦችም ላይ ተጽእኖ የሚሳድር መሆኑን የሚገልጽው ናሆም የሚደረሰውን ጉዳት ስንመለከተው ሰፊ ጉዳት ነው የሚያደርሰው ብሏል።  እንደ ሀገርም የሀገርን ገጽታን ይጎዳል ሲል የገለጸው ናሆም በአንድ አካባቢ ላይ ግጭት ካል የውጭ ሀገራት ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ ክልከላ ያደርጋሉ ይህም የቱሪስት ፍሰቱን በመቀነስ ተጽእኖ ያሳድራል ብሏል።

የቱሪዝም ዝርፉ በረካታ ጠቀሚታ እንዳለው የሚናገረው ናሆም ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠማት ጠቅሶ ዝረፉ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ርገድ ከፍተኛ ሚና እንዳልው አስረድቷል። ነገር ግን በሰላም እጦት ምክንያት ኢትዮጵያ ክቲሪዝም ዘርፉ ማግኘት ያለባትን ገቢ እያገኘች አልምሆኑን የታላቂቷ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር አባል እና ፕሌዥር ኢትዮጵያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ድርጅት ባለቤት ናሆም ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

በአፍሪካ በቀዳሚነት ደረጃ ላይ ያስቀመጡን በርካታ በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰስ ቅርሶች እያሉን   እንደ ሀገር ያልንን የቱሪዝም ሀብት መጠቀም አለመቻላችን እጅም በጣም የሚያስቆጭ ነው የሚለው ናሆም በግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ሳቢያ በመዳረሻዎች ላይ ኢንቭስት የሚያደርጉ ቱሪስቶችን ጭምር እያጣን ነው ሲል በቁጭት ተናግሯል።

እንኳን በሀገር ደረጃ የሚቀሰቀስ ግጭት ሰፈር ውስጥ የሚነሳ ግጭት እንኳ እንቅስቃሴን ይገድባል የሚለው ናሆም በትግራይ ጦርነት ወቅት በረካታ ሀገራት ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ክልከላ ማደረጋቸወን ያሰታወሰው የዘረፉ ባለሙያው አሁንም በአማራ ክልል እየተካሄድ ባለው ግጭት ምክንያት የጉዞ ክልከላ እየተደረገ ይገኛል ብሏል። 

ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ የተቀሰቀሱ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ባስከተሉት ትጽእኖ ሳቢያ በረካታ አስጎብኝ ድርጅቶች ተዘግተዋል፣ ለበርካታ አምታት ኢትዮጵያን ሲያስተዋውቁ፣ ሲያስጎበኙ እና ገጽታን በመገንባት ሲሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች ከዘረፉ ወጥተዋል ብሏል።

በመሆኑም መንግስት ጦርነት፣ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ዘርፉ ላይ እያደረሱ ያሉትን ትጽእኖዎች በመረዳት ወደ ሰላምና መረጋጋት መምጣት እንዲቻል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቀረቧል።

ትኩርቱን ሀገረን በማሰተዋውቅ ጎብኚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማመጣት ላይ አድርጎ እየተንቀሳቀስ ያለው የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍጹም ገዛኀኝ በኢትዮጵያ በሚፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ የቱሪስቶች ቁጥር በእጅጉ መቀነሱን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። እንድ አቶ ፍጹም ገለጻ በጣም የትንጠባጠቡ ቱሪስቶች ናቸው ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ያሉት።  ይህንንም  አነስተኛ ጎብኚዎችን ማግኘት የተቻለው አንዳንድ ድረጀቶች ሰራ ለለምፍታት ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ እና ሃላፊነት እኛ እነወስዳለን እያሉ በሚያደረጉት ጥረት  መሆኑን ጠቅሰዋል። 

አቶ ፍጹም በኢትዮጵያ ላይ የወጡ የጉዞ ክልከላዎች ቱሪስቶችን የኢንሹራንስ ከለላ ስለሚያሳጣ ጎብኚዎች እንዳይምጡ ማድርጉን ጠቀሰው መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የኢትዮጵያን የቱሪስት ፍሰት እንዳልቀነሰ አስመስለው “ለገበያቸው ጥቅም” የሚያወጡት ሪፖርቶች ትክክል አልምሆናቸውን  ተናግረዋል። 

አስጎብኝ ደረጅቶችን በማሰተባበረ በቱሪዘም ዘረፉ ያሉ ችገሮችን ለመቅረፍ እየተንቀሳቀስ ያለው የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር ዳይሬክተር፣ በአሁኑ ውቀት የቱሪዝም ኢንደስትሪው ክባድ ፈተና ወስጥ መሆኑን ገልጸዋል። ከተጀመረ ከ50 በላይ አመታት ያሰቆጠረው ዘርፉ አሁን እንዳጋጠመው አይነት ፈተና ገጥሞት እንደማያወቅም ለአዲስ ስታንዳርድ አስረደተዋል። 

አብዛኛ ባህላዊ፣ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ መስህቦችን የያዙ አካባቢዎች ላይ የሰላም እጦት መኖሩን የጠቆሙት አቶ ፍጹም በዚህም ምክኛት በዘረፉ ላይ ተሰማረተው የሚተዳደሩ ሰዎች ስራ አጥ በመሆን እየተቸገሩ ነው ብለዋል።  ከቱሪዘም ዘረፍ ተጠቃሚው ከላይ አንስቶ እስከ ታችኛው ማህበረሰብ ክፍል ድረስ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፣ ግጭቶች እና አለመረጋግቶች የቱሪዝም ዘረፉን እንቀሰቃሴ በማስቆማቸው የስራ አጥን ቁጥር በእጅጉ እንደጨመረው ተናግረዋል።  በተጨማሪም ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሬን እያሳጣት መሆኑ እንደ ሀገር የሚያደረሰው ተጽዕኖ እና ጉዳት ቀላል አለመሆኑን አስረደተዋል። ይህም ከባድ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ያስገባል ሲሉም አሳስበዋል። 

ቱሪዝም ከኤክስፖረት ዘረፍ ዉስጥ የሚካተት መሆኑን የገለጹት አቶ ፍጹም የቱሪዝም እንቅስቃሴ ቆመ ማለት፣ ኢትዮጵያ እንደ ቡና፣ የቅባት እህሎችን ወደ ውጭ መላክ ባትችል ከሚያስከትለው ቀውስ ጋር የሚነጻጸር ቀውስ የሚያስከትል መሆኑን አስረደተዋል። 

“ፈረንጅ ብቻ ለይቶ የሚምታ ጥየት የለም” ያሉት ዳይሬክተሩ አቶ ፍጹም በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች የሚሰተዋሉት ግጭቶች የሀገረ ውስጥ ጎብኚንም ጭምር የሚያሳጣ  መሆኑን ተናግረዋል። ስጋቶችን ለማጥፋትና ዘረፉን ለማሳደግ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እነደሚገባ ገለጸዋል። “ሁሉም የተጋጩ ወገኖች ወደ ውይይት በመምጣት መፈትሄ ያበጁ” ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል። 

እነዚህ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ግጭቶች፣ ቱሪዝም ሲነሳ ስሙ አብሮ የሚነሳውን የሆቴል ንግድ ዘርፍ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያደስ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአዲስ አበባ እና በቱሪስት መዳረሻ የሚገኙ ሆቶሎች ለጉብኝት ወደ አገር ውስጥ ከሚመጡ ጎብኚዎች የሚያገኙትን ገቢ አሁን ላይ እያገኙ አለመሆኑን ይገልጻሉ። 

የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴሎች ማረኬት ማሀበር ፕሬዘዳንት አቶ ጌታሁን አለሙ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዘርፉ በግጭት ወቅት ጉዳት እንደሚደረሰበት ጠቅሰው ነገር ግን ከዚህ ባልተናነስ ሁኔታ “የዲፕሎማቲክ ጦርነት” ትጽዕኖ እያደረስ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንንም ሲያስረዱ “በትግራይ ጦረነት ወቅት የተለያዩ አገራት ኢምባሲዎች አዲስ አበባ ተከባለች አይሮጵላናችሁ አየር ላይ ሊመታ ይችላል በሚል ፕሮፖጋንዳ ጎብኚውን ስጋት ውስጥ ከተዋል፤  እንደዚህ አይነተ ነገሮች ቱሪዝሙን ሰብሮ ይገድለዋል” ብለዋል። እንደማሀበሩ ፐሬዝዳንት ገለጻ፣ የሰሜኑ ጦረነት ቱሪዝሙን መጉዳቱ ጥርጥር ባይኖረውም የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡ ግን በበለጠ ጉዳት አድርሷል። 

አቶ ጌታቸው ለሆቴሎች ኮከብ አለመሰጠቱን ጠቅሰው ይህም የቱሪስት ፍሰቱን ከጦረነት በበለጠ ይጎዳዋል ብለዋል። “ሆቴሎችን የሚቆጣጠር እና የሚገመግም አካል የለም” የሚሉት ፕሬዝዳንቱ የሆቴሎች ኮከብ ከታደስ አምስት አመታት ማላፋቸውን ገለጸው ካዛሬ አምስት አምታት በፊት ባለ አምስት ኮከብ የነበረ ሆቴል ዛሬ ቢገመገም ባለ ሁለት ኮከብ ሊሆን የሚችል በመሆኑን አስረድተዋል።  መንግስት ይህን ማስፈጸም አልቻለም ሲሉ የገለጹት አቶ ጌታቸው ይህ መሆን እንደሌለበት አሳስብዋል። 

በሌሎች አካባቢዎች አለመረጋጋቶች የሚስተዋሉ በመሆኑ ማህበሩ አሁን ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራን ያለው ደቡባዊ የአገሪቷ ክፍል ላይ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። “ደቡብ ላይ በረካታ የቱሪስት መዳረሻዎች አሉ፣ ትኩረታችን በሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ብቻ መሆን የለበትም፣ ግጭት ያለበት አካባቢ ሰላም መሆኑ አይቀረም፤ አንዱ አካባቢ ስላም ባይሆንም  ሰላም ወደ ሆነበት አካባቢ ላይ መስራት ይገባል፤ ይህ የቱሪስት ፍሰቱ እንዳይቋረጥ ያደርጋል” ሲሉ ገልጸዋል። 

የትግራይ ጦረነት ከተቋጨ በኋላ በአማራ ክልል ባህርዳር፣ ላሊበላ፣ ወሎ አካባቢ ያሉ ሆቴሎችን በቦታው በመገኘት ስልጠና በመሰጠት እና በማደራጀት ወጤታማ እንዲሆኑ አድረገን ነበር ያሉት የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴሎች ማረኬት ማሀበር ፕሬዘዳንት አቶ ጌታሁን አለሙ በአሁኑ ወቀት በአማራ ክልል ቱሪስቱ ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ጭምር መንቀሳቀስ የማይችልበት ሁኔታ ላይ መሆኑን ጠቀሰዋል። በክልሉ ያለው ግጭት ሲያበቃ ሆቴሎቹን በድጋሜ እንደሚያደራጁም ነው የገለጹት።

ግጭት እና ጦርነት ተከስቶ ይቅርና ወረርሽኝ እንኳ ሲከሰት የሆቴል ኢንደስተሪው ይጎዳል ያሉት ፕሬዘዳንቱ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በሚካሄዱት ግጭቶች ምክንያት ጎብኚዎች ስጋት ስለሚገባቸው ወደ ክልሉ ተጉዘው ጉብኝት በማደረግ ላይ አለመሆናቸውን አረጋግጠዋል። 

በዚህ ጉዳይ ላይ የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትግራይ ቱሪዝም ቢሮ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው አስታየታቸውን ማካተት አልቻልንም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button