ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ዮሐንስ ቧያለው፣ ክርስቲያን ታደለ፣ እስክንድር ነጋና ዘመነ ካሴ ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19/2016 ዓ.ም፡- ዮሐንስ ቧያለውና ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ። ክሱን የመሰረተው የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ነው።

ዓቃቤ ሕግ የሽብር ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው መካከል ዮሐንስ ቧያሌው ፋሪስ፣ ክርስቲያን ታደለ ጸጋዬ፣ ካሳ ተሻገር (ዶ/ር) ፣ በላይ አዳሙ፣ ጫኔ ከበደ፣ እስክንድር ነጋና ዘመነ ካሴ እንደሚገኙበት ፋና በዘገባው አመላክቷል።

ክሱ የተከፈተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገመንግስት እና በህገመንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸመ ወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት መሆኑንም ተጠቁሟል።

በተከፈተው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተገለጸው፤ ተከሳሾች የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የሚለው ይገኝበታል ያለው ዘገባው ተከሳሾች ያደራጁትን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሰብስበዉ በመደራጀት፤ የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር በአንድነት የሀገር ባለቤት ሆኖ እያለ “ሀገር ተወስዶበታል ርስቱን ተቀምቷል ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶች እና እሳቤ ብቻ አልተዳደረችም” የሚል አቋም በመያዝ የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸዉን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስና ሀገርን ‹‹በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት›› በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል የሚል እንደሚገኝበት አስታውቋል።

በአጠቃላይ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ተካፋይ በመሆን እና ድርጊቱ የሚሰጠውን ውጤት የራሳቸው በማድረግ የሽብር ቡድን በማደራጀት፣ በማስታጠቅ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ ሎጂስቲክ በማሰባሰብ ተንቀሳቅሰዋል መባላቸውን ያመላከተው ዘገባው እንዲሁም የሽብር ቡድኑ የፕሮፖጋንዳ ልሳን በመሆን መንግስትን በሀይል ከስልጣን ለማውረድ በማሰብ በክልሉ ሰላምን ለማረጋጋት በሚንቀሳቀሰው መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ በክልሉ የፀጥታ አካላት እና ሰላማዊ ህዝብ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገዋል የሚልም እንደሚገኝበት ጠቁሟል።

በጥቃቱ ከ1 ሺህ 100 በላይ በፀጥታ እና በሲቪል ሰው ላይ የሞት፣ ከ600 በላይ በፀጥታ እና ሲቪል ሰዉ አካል ላይ የከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል የሚል ሀሳብ በክሱ ላይ መመስረቱንም አመላክቷል።

በተጨማሪም ከ5 ሺህ በላይ የተለያዩ ዓይነት የጦር መሳሪያዎች፣ ከ600 ሺህ በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች፣ ከ10 ሺህ በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ካዝናዎች፣ በርካታ የመገናኛ ሬድዮኖች እና የጦር ሜዳ መነፅሮች የዘረፉ፣ እንዲዘረፉ እና እንዲወድሙ ማድረጋቸውን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ዝርዝር መግለጹን አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ማለትም በሞጣ፣ ብቸና፣ ቦረና፣ ባህርዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረማርቆስ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደባርቅ፣ አዲስ ዘመን እና ጋይንት ማረሚያ ቤቶች ላይ ጥቃት በማድረስ ከ5 ሺህ 689 በላይ ታራሚዎች እንዲያመልጡ እና በማረሚያ ቤት ላይ ከ123 ሚሊዮን 590 ሺህ 282 ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስበት አድረገዋል የሚል የክስ ሀሳብ መመስረቱንም አስታውቋል።

ከ90 በላይ የመንግስት እና የግለሰቦች መኪኖች እንዲዘረፉ እና እንዲወድሙ እንዲሁም ለአርሶ አደር የሚከፋፈሉ ከ9 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ የዘረፉ እና እንዲዘረፉ ያደረጉ በመሆኑ የሚል ክስም እንደተመሰረተባቸው አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button