ዜናፖለቲካ

ዜና: ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ተቋም (RSF) ማለቂያ የሌለው ሲል የገለጸውን የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን የማሰር ተግባር ኮነነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለውን ግጭት የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ከማሰር ተግባሩ እንዲቆጠብ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ተቋም (RSF) መጋቢት 12 ቀን 20016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።

በሁለት ጋዜጠኞች የተመሰረተው ኢትዮኒውስ የዩትዩብ ቻናል፣ መስራቾቹ ለእስር እና ለስደት መዳረጋቸውን የጠቀሰው ተቋሙ መንግስት በአማራ ክልል በፋኖ ጣታቂዎች እና በመንግስት ሀይሎች መካከል የሚካሄደውን በትጥቅ የተደገፈ ግጭት በመዘገባቸው፣ በላይ ማናየ እንዲታሰር ማድረጉን ሌላኛው መስራች በለጠ ካሳ መኮንን ደግሞ መሰደዱን አስታውቋል።

190 ሺ ተከታዮች ባሉት በኢትዮኒውስ ዩትዩብ ቻናል የተፈጸመው ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት “ማለቂያ የሌለው” ነጻ ሚዲያዎችን የማፈን ተግባሩን መቀጠሉን ማሳያ ነው ብሏል።  

የኢትዮ ኒውስ ቻናል አንደኛው መስራች በላይ ማናየ ከአማራ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአዋሽ አርባ የወታደራዊ ካምፕ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተቋሙ አስታውቋል። በአዋሽ አርባ የእስረኞች ማቆያ በተከሠተ አውሎ ማናየ ጉዳት ማስተናገዱን የጠቆመው አርኤስኤፍ ተገቢ ህክምና እንዳላገኘ ስማቸው እንዲገለጹ የጠየቁ ሶስት ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።

ኢትዮኒውስ ቻናል መንግስት በአማራ ክልል ግጭት ዙሪያ ዘገባ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን ማሰር መቀጠሉን ማሳያ ነው፣ አንዳንዶቹ በመዲናዋ በሚገኙ እስር ቤቶች፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በረሃማ በሆነው የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው የአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው ይገኛሉ፣ ሌሎች ደግሞ ከሀገራቸው እንዲሰደዱ ተደርገዋል ሲሉ የተቋሙ የሰሃራ በታች የአፍሪካ ዳይሬክተሩ ሳዲቦ ማሮንግ መግለጻቸውን አመላክቷል።

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ተቋም (RSF) የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን የማሰር ተግባር ማለቂያ የሌለው ሲል በመግለጽ ነው የኮነነው። እስኪዘጋ ድረስ 190ሺ ተከታዮች እንደነበረው የጠቆመው ተቋሙ የቻናሉ ሌላኛው መስራች በለጠ ካሳ መኮነን ከመንግስት የሚደርስበት ጫና ስለበረታበት እና ለሂወቱ በመስጋት ከሳምንታት በፊት ሀገሩን ጥሎ መሰደዱን ጠቁሟል። በለጠ ሲቪል የለበሱ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ክትትል ያደርጉበት እንደነበር እና የእስር ትዕዛዝ እንደወጣበት ከምንጮቹ መስማቱን በተመለከተ ሪፖርት አድርጎ እንደነበር የተቋሙ መግለጫ አስታውሷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button