አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19/2015 ዓ.ም፡- በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት የትግራይ ሴቶችን ከመደፈር አላዳናቸውም፣ በርካታ የክልሉ ሴቶች ከፕሪቶርያው ስምምነት በኋላ ተደፍረዋል ሲል አንድ ጥናት አስታወቀ።
ትላንት ነሃሴ 18 ቀን 2015 ይፋ የተደረገው ሐኪሞች ለሰብአዊ መብት እና የአፍሪካ ቀንድ ፍትህ እና ተጠያቂነት ድርጅት (Physicians for Human Rights and the Organization for Justice and Accountability in the Horn of Africa) በጋራ ይፋ ያደረጉት ጥናት እንደሚያመላክተው 128 የሚሆኑ የትግራይ ሴቶች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ መደፈራቸውን ገልጿል። ጥናቱ ያካሄዱ የተቋማቱ ባለሞያዎች በክልሉ ከሚገኙ ህክምና ማዕከላት ያሰባሰባቸው 304 ከሚሆኑ የህክምና ማስረጃዎች መካከል 128 የሚሆኑት የአስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸው ሁነው መግኘታቸውን አስታውቀዋል።
የሰላም ስምምነቱ በክልሉ የተካሄደውን ጦርነት ቢያስቆመውም በሁሉም ተዋጊ ሀይሎች በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት ግን ማስቆም አልቻለም ሲል የተቋማቱ ጥናት አሳስቧል።
በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት የተደረሰው የሰላም ስምምነት ከፌደራል መንግስቱ ጎን ተሰልፋ ስትዋጋ የነበረችውን ኤርትራን አለማካተቱን ያስታወቀው ጥናቱ አስገድዶ መደፈር የደረሰባቸው ተጎጂዎች ጥቃቱን የፈጸሙባቸው በኤርትራ ከሚደገፉ ታጣቂዎች መሆኑን ማመላከታቸውን አስታውቋል።
ጥናቱ ካካተታቸው መካከል 76 በመቶ የሚሆኑት በሶስት እና ከዚያ በላይ ወንዶች መደፈራቸውን እንደሚያሳይ አስታውቆ 94 በመቶ የሚሆኑት ሲደፈሩ ያለኮንዶም መሆኑን ጠቁሟል።
ከተደፈሩት ሴቶች መካከል በርካታ ልጃገረዶች ለተደጋጋሚ ጾታዊ ግንኙነት ጥቅም ሲባል በታጣቂዎቹ በጠለፋ መወሰዳቸውን ጥናቱ አመላክቷል። በጥናቱ የተካከቱት እጅግ ብዙ ወንጀል ከተፈጸመባቸው የትግራየ ሴቶች መካከል እጅግ አናሳው ነው ሲል የተቋማቱ ይፋ ጥናት ገልጿል።
ፍትህ በአስገድዶ መደፈር እና በጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ዋነኛ መገገሚያ ተደርጎ እንደሚወሰድ የጠቆሙት ተቋማቱ የትግራይ ሴቶችን ግን ይህንን እንዳያገኙ ተከድተዋል ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተፈጸመውን ግፍ እንዳይጠና ውሳኔ ማሳለፉን በአብነት አስቀምጠዋል የአፍሪካን ህብረት ውሳኔንም ፖለቲካ ዊ ውሳኔ መሆኑነ ገልጸው ህብረቱ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚደርስበትነ ጫና ለመቋቋም ሲል ያሳለፈው ነው ሲሉ ኮንነዋል። አስ