ዜና

ዜና፡ ኢትዮጵያ ቢትኮይኝ ማይኒንግ ያስጀምራታል የተባለ ስምምነት ከሆንግ ኮንግ ኩባንያ ጋር ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8/ 2016 ዓ/ም፡_ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከሆንግ ኮንግ ዳታ ማዕከል አገልግሎት ጋር  የ250 ሚሊዮን ዶላር  የመረጃ ማይኒንግ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠና ስምምነት ተፈራረመ።  

ኢትዮጵያ ከሆንግ ኮንግ የዳታ ኩባንያ ጋር የፈጸመችው ስምምነት የቢትኮይን ማይኒንግ እንደሚያካትት ኮይን ቴሌግራፍ ዘግቧል። 

በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያለው የኢንዶኔዢያው ሃሽላብስ ማይኒንግ ስራ አስኪያጅ ቃል ካሳ በኤክስ ማህባራዊ ትስስር ገጻቸው “ የኢትዮጵያ መንግስት ከሆንግ ኮንጉ ከዳታ ሲንተር ሰርቪስ ኩባንያ ጋር በፈጸመው ስምምነት ቢትኮይን ማይኒንግ ያከናውናል” ብለዋል። 

የኢትዮጵያ እና የሆንግ ኮንጉ ኩባንያ ስምምነት በኢትዮጵያ ለዳታ ማይኒንግ መሰረተ ለማት ዝርጋታ እና ለስው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠና የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላይ ፕሮጀክት ትብብር ስምምነት መሆኑ ተገልጿል። 

ቢትኮይን ማለት የዲጂታል ገንዘብ ስርዓት ሲሆን ግብይቱ የሚከናውንውም በኢንተርኔት አማካኝነት ነው። በቢትኮይን ግብይት ውስጥ ምንም አይነት በእጅ የሚጨበጥ ገንዘብ የለም።  ክሪፕቶከረንሲም የኢትንተርኔት ወይም የበይነ መረብ ላይ መገበያያ ነው። 

እንደ ኮይን ቴሌግራፍ ዘገባው ከሆነ ኢትዮጵያ ለማይኒንግ ፍቃድ የሰጠችው በ2022 ሲሆን ከዚሁ አመት ጀምሮ የኢንዶኔዥያው ሃሽላብስ ማይኒንግ በስራ ላይ ነው። የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ግን በኢትዮጵያ ተከልክሏል። 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስምምነቱ ክሪፕቶማይኒንግ ስለማካተቱ አልጠቀሰም። ብሉምበርግ በዘገባው ኢትዮጵያ የክሪፕቶማይኒንግ ፍቃድ ለመስጠት ጥናት እያደረገች መሆኑን ማስታውቁ ይታወቃል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሪፖርቶች እንድሚያሳዩት በኢትዮጵያ 21 የክሪፕቶ ማይኒንግ ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 19ኙ የቻይና ድርጅቶች ናቸው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button