ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች መከላከያ ሰራዊት ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወስዳል -  የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27/ 2016 ዓ/ም፦ የፌዴራል መንግስት ትላንት በሰጠው መግለጫ ፤ በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች “የወሰን እና የማንነት” ጥያቄዎች በህዝበ ውሳኔ እልባት እስኪያገኙ ድረስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው መህበረሰብ ጋር በመሆን ሰላም እና ደህንነት እንደሚቆጣጠር ገለጸ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፤ “ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በኩል በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየው አዝማሚያ ተገቢነት የሌለው ብቻ ሳይኾን የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። 

ሚኒስትሩ አክለውም፤ የሚነሱ ጥያቄዎችን እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይት እና በድርድር ከመፍታት ይልቅ “ወሰንን በኃይል እናስከብራለን” የሚል አካሄድ ካለፈው ስሕተት አለመማርን ያመለክታል ነው ብለዋል፡፡ “ሰላሙን እያጸና የሚገኘውን የትግራይ ሕዝብ ለሌላ ዙር ስቃይ እና እንግልት የሚዳርግ” መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ለገሰ በመግለጫቸው፤ የፌዴራል መንግስር የማንነት እና ተወሰን ጥያቄን በህዝበ ውሳኔ እንዲፈታ ግልጽ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገለጸው፤ “ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ ለጊዜው ትርፍ የሚያስገኝ ቢመስልም ዘላቂነት አይኖረውም ” ብለዋል። 

ከፌዴራል እና ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጣው ዐቢይ ኮሚቴ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡

ተፈናቃዮችም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ቀያቸው መመለስ ይኖርባቸዋል ያሉት ቃል አቀባዩ “በአካባቢው ህዝብ ምርጫ” የአካባቢው አስተዳደሮች መመስረት ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል። ሁኔታው ሲረጋጋም ምርጫ ቦርድ በገለልተኝነት ህዝበ ውሳኔ ያካሄዳል ብለዋል። 

ሁለቱም ክልልች ይህን አቅጣጫ እንዲያከብሩ እና በአካባቢው ላለው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተጨማሪም በሁለቱ ክልሎች ሰላም እና መረጋጋት እንዳይመጣ የጽንፈኛ ኃይሎች የዘረጉትን ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር ለመቆጣጠር ሁለቱም ክልሎች መቆጣጠር አለባቸው ነው ያሉት፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button