ዜና

ዜና፡ ከንግድ ባንክ በወሰዱት ገንዘብ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች የሚመልሱት ገንዘብ ባለመኖሩ ጭንቅ ላይ ናቸዉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/2016 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነ ብር በማውጣት ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች፤ ገንዘቡ መመለስ አለበት መባሉን ተከትሎ ጭንቅ ላይ ናቸዉ ተባለ።

ባንኩ ከባንኩ ገንዘብ ያለአግባብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም. ድረስ ክቅርንጫፎች በተጨማሪ በዲጂታል የክፍያ አማራጭን በመጠቀም ገንዘቡ ያለአግባብ ወጪ ወደተደረገበት በባንኩ የሚገኝ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፍ እና ገቢ እንዲያደርጉ አስጠንቅቋል

በቀነ ገደቡ ያልመለሱትን ግለሰቦች ስምና ፎቶ በመገናኛ ብዙኃን ይፋ በማድረግ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርግም አስጠንቅቋል።

ይህን ተከትሎ፤ በድንገት እጃቸው ላይ የገባውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ የተለያዩ እቃዎች የገዙበት ወይም ከንግድ ባንክ አካውንታቸው ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ያዘዋወሩ ተማሪዎች ከፍተኛ “ጭንቀት” ላይ እንደሚገኙ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

በተለይ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች ጥቂት አለመሆናቸውን የሚጠቅሰው ቢቢሲ ያነጋገረው የ #ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ “100ሺህ ብር የወሰደ አንድ ልጅ በሁለተኛው ቀን ላፕቶፕ እና ስማርት ስልክ” በመግዛቱ እጁ ላይ የሚመልሰው ገንዘብ እንደሌለ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተፈጠረው ችግር የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የወሰዱ ተማሪዎች ሂደቱን “ሥራ” በሚል ቃል ነበር የገለጹት።

ተማሪው፤ “እኔ ወደ 150 ሺህ ብር ሠርቻለሁ። 300 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ የሠሩ ተማሪዎች አሉ። . . . ቀድሞ የሰማ [የሲስተም ብልሽቱን] ብዙ ሠርቷል” ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ተማሪው አክሎም በዕለቱ “ ሁሉንም ብር ተመላሽ አድርጊያለሁ። ወደ ሌላ ባንክ ያዘዋወሩ ጓደኞቼ ግን ጭንቀት ላይ ናቸው” ሲል የተፈጠረውን ሁኔታ ገልጿል።

ቢቢሲ ያነጋገረው ሌላኛው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ 70 ሺህ ብር በሞባይ ባንኪንግ መውሰዱን አምኖ የወሰደውን ለመመለስ ፍቃደኛ ቢሆንም አካውንቱ በመታገዱ ተመላሽ ማድረግ አለመቻሉን ይገልጻል።

ቀነ ገደቡም ነገ በመሆኑ ገንዘቡን ወስደው የተጠቀሙበት እንዲሁም ወደ ታገዱ አካውንቶች ያዘዋወሩ ተማሪዎች “ድንጋጤ እና ጭንቀት” ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከባንኩ የወሰደውን ገንዘብ ወደ ሌላ አካውንት አዘዋውሮ ገንዘቡን ለመመለስ ተቸገርኩ ያለ ተማሪ በቅርቡ ፈተና እንዳለበት እና “ከክስተቱ ጋር በተያያዘ የስሜት መረበሽ ውስጥ እንደሚገኝ” ገልጿል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button