ዜናፖለቲካ

ዜና፡ “በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት የማኅበረሰቡ መገለጫ የኾኑ የጋራ ትስስር እሴቶች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል” – ርዕሰ መስተዳድሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21/2016 ዓ.ም፡- ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በተገኙበት የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ከክልሉ ባለሃብቶች ጋር በሰላም እና ልማት ዙሪያ ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ ባለፉት ስምንት ወራት በነበረው ግጭት ከፍተኛ የሰብዓዊ ጉዳት እና የክልሉ ሕዝብ ሃብት የኾኑ ንብረቶች መውደማቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የማኅበረሰቡ የረጅም ዘመናት የማንነት መገለጫ የኾኑ የጋራ ትስስር እሴቶች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ሲሉ ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ምክክሩ በአማራ ክልል የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ባለሃብቶች ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋ ከበደ በመክፈቻ ንግግራቸው መግለጻቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ የጋራ ትርክት ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ መልእክት አስተላልፈዋል ያለው ዘገባው “ባለሃብቶች በአማራ ክልል ያለውን እምቅ ሃብት ተጠቅመው በማልማት ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባቸዋል” ማለታቸውንም አስታውቋል።

በክልሉ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ሥርዓቶችን ተጠቅሞ መቅረፍ እንደሚገባ በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙ የክልሉ ባለሃብቶች ገልጸዋል ያለው ዘገባው ክልሉ ባለፉት ሦስት ዓመታት በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም አሁን ባለው ግጭት ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ እንዲደርስበት ምክንያት መኾኑን አንስተዋል ብሏል።

የአማራ ክልልን የሰላም መደፍረስ ለመፍታት መንስኤውን ለይቶ ማወቅ እና ለችግሩ መፍትሄ ማምጣት ከአመራሩ የሚጠበቅ መኾኑንም ተናግረዋል ያለው የአሚኮ ዘገባ ከክልሉ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ውይይትን እንዲያስቀድም መጠየቃቸውን ጠቁሟል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button