ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ በሙስና ወንጀል በተከሰሱ 175 ግለሰቦች እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30/ 2016 ዓ/ም፡_ በግማሽ አመቱ በፍርድ ቤት ክርክር ሲደረግባቸው ከነበሩ 489 መዛግብት መካከል በአንድ መቶ መዝገቦች የተከሰሱ 175 ግለሰቦች ጥፋተኛ ተብለው እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የተቀጡ መሆናቸውን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት፣ ከፓስፖርት እና ሌሎች አገልግሎቶች አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሲፈጸም በነበረ የሙስና ወንጀል ላይ በተሰራ ህግ የማስከበር ተግባር ኢትዮጵያውያን ብቻ ማግኘት የሚገባቸውን የኢትዮጵያን ፓስፖርት በሺዎች የሚገመት ዶላር እና የኢትዮጵያ ብር በመቀበል ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ዜጎች ፓስፖርት በመስጠት ከየአንዳንዱ አገልግሎት ፈላጊ ከ10 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር በመቀበል ሲያስፈጽሙ በነበሩ ምርመራ ተጣርቶ በድምሩ 60 ተጠረጣሪዎች ላይ 15 ተደራራቢ ክሶች መቅረባቸው ተገልጿል። 

ሚኒስቴሩ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሾች በወንጀል ድርጊቱ ያፈሩትን ሃብት በተመለከተ ሰፊ የምርመራ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ እና ቀሪ የወንጀል ምርመራው እንዳለቀ ውሳኔ የሚሰጠበት ይሆናል ማለቱን  አቢሲ ዘግቧል።  

ከመሬት ጋር በተያያዘ መብት ሳይኖራቸው በተጨበረበረ መንገድ ከብር 82,960,000 በላይ የሚገመት ምትክ ቦታ እና ካሳ በወሰዱ እና በሰጡ፣ የመሬት ጉዳይን እናስፈጽማለን በማለት ስምንት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ በተቀበሉ እና በሌሎችም የመሬት ጉዳይ በደመሩ 48 ተከሳሾች ላይ ከባደ የሙስና ወንጀል እንዲሁም በህገ ወጥ መንገደ የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ በማቀረብ ወንጀል ክስ ተጠቅሷል። 

በባንኮች ላይ በሚፈጸም ምዘበራ እና ማጭበርበር ጋር በተያያዘም ከተለያዩ ባንኮች ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ በወሰዱ የባንክ ሰራተኞች ላይ እና ሌሎች ግለሰቦች ላይ በ14 የተለያዩ መዘገቦች ክስ ማቀረብ ተችሏል ተብሏል።

በአሁኑ ግዜ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መካከል አንዱ ሀሰተኛ የመንግስት ሰነዶችን ከማዘጋጀት እና ከመገልገል ጋር በተያያዝም ሀሰተኛ የመንግስትና የህዘባዊ ደርጅቶች ሰነዶችን በማዘጋጀት እና ለተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት በማቅረብ ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ በወሰዱ ግለሰቦች ላይ በ12 መዝገቦች ክስ እንደቀረበባቸውም ተገልጿል። 

ከዚህም በተጨማሪ በግማሽ አመቱ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ የልማት ተነሺ ሳይሆኑ እንደሆኑ በማስመሰል በተጭበረበረ መንገድ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በወሰዱ እና እንዲከፈል ባደረጉ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚን ጨምሮ 16 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው እስከ 19 አመት ጽኑ እሰራት ተወስኖባቸዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button