ዕለታዊፍሬዜናቢዝነስ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ መንገድ ከአገር በሚወጣ የቁም እንስሳት በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ ታጣለች ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19/ 2016 ዓ/ም፡ ኢትዮጵያ በቀን ከ1 ሺህ 200 በላይ የቁም እንስሳት በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር በመውጣታቸው በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ እንደምታጣ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ገለፀ።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት  ሕገ-ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ትላንት አካሄዷል። ምክር ቤቱ ሕገ-ወጥ ንግድ በስፋት በሚታይባቸው ዘርፎች ላይ ያካሄዳቸውን ጥናቶችም ይፋ አድርጓል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት ከቁም እንስሳት ንግድ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ እየቀነሰ መምጣቱን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለባቸው ገልጸዋል።

ለማሳያም ቀደም ሲል ከዘርፉ እስከ 150 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ይገኝ እንደነበር አስታውሰው፤ በ2014 ዓ.ም እና በ2015 ዓ.ም ገቢው ወደ 17 ሚሊየን ዶላር መቀነሱን አስረድተዋል።

የችግሩ ምንጭም የሕገ-ወጥ ንግድ ስልትና ዓይነት እየተቀያየረ መምጣቱ፣ የክትትልና የቁጥጥር ሥራው አጥጋቢ አለመሆኑ፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈና ሕጉን የጠበቀ የግብይት ሥርዓትን ማስተግበር ላይ ክፍተቶች መኖራቸው መሆኑን ተመላክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የቁም እንስሳት ልየታና ከተቀባይ አገራት ጋር ያለው ሕጋዊ ስምምነት ላይም ክፍተቶች እንደሚታዩ አንስተዋል።

በመሆኑም በቅርቡ በአገሪቱ በሦስት የመውጫ በሮች በተካሄደ ጥናት በቀን ከ1 ሺህ 200 በላይ የቁም እንስሳቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገር እንደሚወጡ ተረጋግጧል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በዚህም አንድ የቁም እንስሳት እስከ 530 ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፤ አገሪቱ በቀን 630 ሺህ ዶላር በላይ በአንድ ወር ደግሞ 19 ሚሊየን ዶላር ታጣለች ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button