ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ “እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም” ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28/2016 ዓ.ም፡- ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ለጠ/ሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ስለተከሰተው ድርቅ እና መንግስታቸው እየሰጠው ስላለው ምላሽ የተመለከተው ይገኝበታል።

ጠ/ሚኒስትር አብይ “እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም” ሲሉ ገልጸው ያለው ችግር በረሃብ ላይ ተጓዳኝ በሽታዎች ተከስተው ያመጡት ነው ብለዋል፤ ወባ ሲጨመር፣ ተቅማጥ ሲጨመር በምግብ እጥረት የተመጣጠነ ምግብ ሲጠፋ እና እላዩ ላይ ሲጨመር መቋቋም አቅቶት ሊሞት ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት አልሰጠውም መባሉን የተቹት ጠ/ሚኒስትሩ መንግስት 15 ቢሊየን ብር አውጥቷል ለተረጂዎች እርዳታ ለማዳረስ ጥረት አድርጓል ብለዋል፤ ልማት ቀንሰን ሰው እንዳይሞትብን አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል። አሁንም እናወጣለን ሲሉ ጠቁመዋል።

በድርቅ ምክንያት ሰው ተርቦ ህይወቱ እንዲያልፍ መፍቀድ የለብንም በሚል ምክንያት ነው ይሄንን ሁሉ የምናወጣው  ሲሉ የተደመጡት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይየኢትዮጵያ መንግስት ፕሮጀክት አጥፎ ህዝቡ በረሃብ እንዳይሞት የሚችለውን ሁሉ ከህዝቡ ጋር በመተባበር ይሰራል ሲሉ አስታውቀዋል።

ድርቅን በተመለከተ ጠ/ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ላይድርቅ ለኢትዮጵያ እንደ ባህላችን እንደ አድዋ ድል መቶ አመት ሲጎበኘን የኖረ ስለሆነ እንደ አዲስ ንግርት የምናወራው ነገር አይደለም፤ ላለፉት መቶ አመታት ድርቅ እንደሚመጣ ብናውቅም በበቂ ደረጃ አምርተን ሰዎች በረሃብ እንዳይሞቱ ማድረግ ተስኖን ቆይተናል ብለዋል።

አሁን በሀገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ ማየት ያለብን እንደ ፖለቲካ አይደለም ሲሉ ያሳሰቡት ጠ/ሚኒስትሩ  የተከበረው ምክር ቤት እንዲለየው የምፈልገው ኢተዮጵያ ውስጥ ዘንድሮ ከምንግዜውም በላይ በታሪካችን አምርተን የማናውቀውን ምርት አምርተናል ይሄንን ምርት አርሶ አደሩ አምርቶ ወንድምህ እየሞተ ነው ቢባል ዝም ይላል ብላችሁ አትጠብቁ፤ መንግስት እንኳ ባያደርግ ሰው ተባብሮ በድርቁ ሰው እንዳይሞት ያደርጋል ብለዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button