ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የፌደራል መንግስት መግለጫ ፀረ ፕሪቶርያ አቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን የሚያበረታታ ነው – የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር

አዲስ አበባ፣ ጥር 28/2016 ዓ.ም፡- የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከፕሪቶርያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ የትግራይ ክልል መንግስት ግዜያዊ አስተዳደር በፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በኩል ምላሽ ሰጠ።

ከፕሪቶርያ ስምምነት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የተሰሩና እስካሁንም ባልተሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ቀጠሮ መያዙን ግዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው ጠቁሞ ከተያዘዉ ቀጠሮ በፊት መግለጫ መውጣቱ ተገቢ ነዉ ብሎ እንደማያምን አስታውቋል።  

ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው ባነሳቸው ጉዳዮችን በሚመለከት ማብራርያ ሰጥቷል።

ግዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው ከበጀትና መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የፌደራል መንግስቱ ከፕሪቶርያ ስምምነት ወዲህ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አወድሷል። መታረም ያለባቸው ጉዳዮች በሚመለከት ለጠ/ሚኒስትሩ ሪፓርት እንደሚያቀርብ በመጠቆም በጉዳይ ዙሪያ በመግለጫው የሚያነሳው ነገር እንደማይኖር አስታውቋል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት “አከራካሪ ቦታዎች” ሲል በገለጸው ጉዳይ ዙሪያ ጉዳዩን በሪፈረንደም ለመፍታት መረዳዳት ተደርሶ ነበር በሚል የቀረበው የመግለጫው ክፍል ፍፁም የተሳሳተ ነው ሲል የተቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከተሰጠን ስልጣን ውጪ የሆነ ተግባር ነው፣ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

ከተፈናቃዮች መመለስ ጋር ተያይዞ “ትክክለኛ ተፈናቃዮች ተመልሰዋል” በሚል ለቀረበው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የመግለጫው ክፍል ጋር በተያያዘ አደገኛ ነው ሲል ገልጾ በጉልበት የሃገሪቱ ካርታ ለመቀየር የፌዴራል መከላለያ ሆነ የጎርቤት ሃገራትን አቅም ተጠቅሞ የተደረገን አውዳሚ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የሚያግዝ ነው ሲል ተችቷል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው “ትክክለኛ ተፈናቃይ” “ትክክለኛ ያልሆነ ተፈናታይ” በሚል ያስቀመጠውን ጭብጥ መፈታት የነበረበትን ችግር የበለጠ የሚያባብስ አደገኛ ትንታኔ ስለሆነ አንቀበለዉም ሲል በምላሹ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የፌደራል መንግስቱ የመፍትሄው አካል መሆን ሲገባ የችግሩ አካል ለመሆን የወሰነ የሚያስመሰለው ስለሆነ በፍፁም ተቀባይነት የለውም ብሏል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው በትግራይ ከተካሄደው ጦርነት ጋር የተገናኙ “ወንጀለኞችን” ተጠያቂ አድርጊያለሁ፣ “ተገቢውን እርምጃም” ወስጃለሁ ማለቱን በተመለከተ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግጫው ፍትህ የማረጋገጥ ተግባር የዘመቻ ጉዳይ እንዳልሆነ ታውቆ ሁሉም ሊሰራበት የሚገባ ነው ሲል ገልጿል።

ፀረ ፕሪቶርያ አቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በተሳሳተ አቋማቸው እንዲገፉበት የሚያበረታታ መግለጫ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ነው ሲሉ የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጫን ተችቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button