ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የቀደሞው የሰላም ሚንስትር ታዬ ደንዳኣ ፍርድ ቤት አለመቀረባቸውንና ከጠበቆች ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን ባለቤታቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5/ 2016 ዓ/ም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰላም ሚንስትር ታዬ ደንዳኣን ከኃላፊነታቸው ማንሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሶስት ቀናት ቢያልፉም እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቀረባቸውን እና ጥብቅና ሊቆሙላቸው ከፈለጉ ጠበቆች ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸው ባለቤታቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።  

የቀደሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት አቶ ታዬ በፌዴራል ከፍተኛ ወንጀል ምርመር ቢሮ ታስረው የሚገኙ ሲሆን ከተያዙበት ቀን ጀመሮ በርቀት ከማየት በቀር ቀርበው ለማነጋገር ፍቃድ ማግኘት አልቻሉም። 

“በቁጥጥር ስር በዋሉበት ቀን የት እንዳሉ ማወቅ አልቻልንም ነበር። በሁለተኛው ቀን ምግብ ይዤ በሄድም ማየት እንደማልችል ተነገሮኝ ተመለሻለው። በሶስተኛው ቀን ወደሚገኙበት እስር ቤት ሄጄ በርቀት አይቻቸዋለሁ፣ ቀርቤ እንዳወራቸው ግን አልተፈቀደልኝም” በለዋል።  

ወ/ር ስንታየሁ አቶ ታዬን ማየት የተከለከሉት ቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ ጥብቅና ሊቆሙላቸው የፈለጉ ጠበቆችም ጭምር እንዳያገኙዋቸው መደረጉን ተናግረዋል። “ብዙ ጠበቆች ጥብቅና ሊቆሙላቸው ፍላጎት አሳይተው አቶ ታዬን ለማግኘት ጠይቀው ነበር፤ ነገር ግን አልተፈቀደላቸውም፣ የፍርድ ቤት ሂደተም አልተጅመረም” ሲሉ አስረድተዋል። 

የሁለት ልጆች አባት የሆኑት የቀድሞው የሰላም ሚኒስትሩ በቁጥጥር ስር በዋሉብት ግዜ ልጆቻቸውን ጨምሮ ስምንት የቤተሰቡ አባላት በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አንደነበሩ አክለው ተናግረዋል።

በመኖሪያ ቤታቸው ሰኞ ዕለት የተደረገውን ፍተሻ በተመለከተ ለአዲስ ስታንዳርድ የገለጹት ወ/ሮ ስንታየሁ “ ሰኞ ከለሊቱ 5 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ድረስ ፍተሻ ሲደረግ ነበር፤ ይህ ሁሉ የሆነው በልጆቻችን ፊት በመሆኑ በልጆቹ ላይ ከባድ የሰነ ለቦና ጫና ደረሶባቸዋል” ብለዋል።

“ልጆቹ አባታችን የት ነው ያለው? ብለው እየጠየቁኝ ነው። ስነልቦናቸው ተጎድቷል። ትምህርታቸውንም አቋርጠዋል” በለዋል ወ/ሮ ስንታየሁ። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አቶ ታዬ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ መንግስት ከሰጣቸው መኖሪያ ቤት ለቀው እንዲወጡ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ትላንት 3 ሰዓት አካባቢ ከቤቱ መውጣታቸውን ገልጸዋል።  

“ለአሁን የተወሰኑ እቃዎችን እና የምንለብሰውን ወስደን ወደ ዘመድ ቤት ተጠግተናል። የቀሩት እቃዎች በሙሉ ከቤቱ ጋር ታሽገዋል” ሲሉ ገልጸዋል። 

በፍተሻው ወቅት በቤታቸው ውስጥ ተገኝተዋል የተባሉትን እቃዎች እና “ከፀረ-ሰላም አካላት ጋር በመንግስት እና በፓርቲያቸው ላይ አሲረዋል” ሲል መንግስት ያቀረበባቸውን ውንጀላ በተመለከተ ወ/ሮ ስንታየሁ “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

“እየቀረበባቸው ያለው ውንጀላ በጣም አስገረሞናል። አቶ ታዬ ለፓርቲያቸው ከፈተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል። እንዲሁም የፓረቲውን መተዳደሪያ ደምብ የሚያከብሩ ሰው ናቸው። የተያዙትን መሳሪያዎች እና የመኪና ታርጋዎችን ሁሉ የሰጣቸው መንግስት ነው። በህገ ወጥ መንገድ እንደያዘው አድርገው መናገራቸው ትክክል አይደለም” በለዋል።

አቶ ታዬ በማህበራው ትስስር ገጻቸው በተደጋጋሚ መንግስትን ሲተቹ የሚስተዋሉ ሲሆን በቅርቡ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ “በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል የተካሄደው የሰላም ድርድር ላለመሳካቱ ምክንያት መንግስት ነው” በማለት መንግስትን ከሰዋል። ይህንን ተከትሎ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከታህሳስ 1 ጀምሮ አቶ ታዬን ከኃላፊነታቸው አንስተዋል።

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ባሳወቀበት መግለጫ “ታዬ ደንደአ ከህዝብና ከመንግስት የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተለይም ደግሞ የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ሆኖ ሰላምን ለማስፈን መሥራት ሲገባቸው፤ በተቃራኒዉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረሰላም ኃይሎች ጋር በመተሳሰር  ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ ተደርሶባቸዋል” ሲል አስታውቋል። ግብር ሃይሉ ተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ ከእገታ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንደአለበት ተደረሶባቸዋል ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button