ዕለታዊፍሬዜና

እለታዊ ዜና፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ ተወካዮች ወደ አማራ ክልል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 1/ 2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በውስጡ ያሉ የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች ተወካዮች ወደ አማራ ክልል ገብተዋል።

ወደ አማራ ክልል ከገቡት ተወካዮች መካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ራሚዝ አልአክባሮቭ (ዶ.ር)፣ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ሚካኤል ሳድ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የሥነ ሕዝብ ድርጅት (UNFPA) ምክትል ተወካይ ያይዎ ኦሉዮሚ፣ የኬር የሀገር ውስጥ ዳይሬክተር ካትሊን ጎጊን እና የተመድ የጸጥታ ዋና አማካሪ ፕሪንስ ብሩስ ይገኙበታል።

ተወካዮቹ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በባሕርዳር ከተማ የፓናል ውይይት ያካሂዳሉ ሲል አሚኮ ዘግቧል።

የተመድ ልዑካኑ በትላንትናው እለት በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የዩኒሴፍ (UNICEF) ፤ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ( UNHCR)፤ ተመድ ሴቶች (UN Women)፣ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (OCHA) ፣ የተመድ የፀጥታ እና ደህንነት (UNDSS)፣ የተመድ ምግብ እና ግብርና ድርጅት (FAO) እና ሌሎች የተባበሩት መንግስታ ድርጅቶች የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በውይይቱ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች የክልሉ መንግስት የግብርና ልማትን ለማሳደግ፣ በውሃ፣ በኢነርጂና በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፎች የሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እና እገዛ ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የክልሉ ሚዲያ አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኃላፊዎቹ ከዚህም በተጨማሪም በክልሉ የተቋረጠውን የምግብ ድጋፎች በማስቀጠል የሰብአዊ አቅርብት ስራዎችን ለማጠናከር ሊሰሩ በሚገቡ ስራዎችም ላይ መክረዋል ተብሏል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button