ዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ ዲፒ ወርልድ የበርበራን ወደብ በጋራ ለማልማት ያሳየውን ፍላጎት እንደምትቀበለው አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 16/ 2016 ዓ/ም፦ በተባበሩት አረበ ኢምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኦማር ሁሴን ዲፒ ወርልድ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሶማሊላንድ በርበራን ወደብ  ለማልማት ያሳየውን ፍላጎት መንግስት እንደሚቀበለው ገለጹ። 

አምባሳደሩ ለኢፕድ  በሰጡት ማብራሪያ ዲፒ ወርልድ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ያሳየው ፍላጎት መንግስት እያሰራበት ያለበት እና ተቀባይነት ያለው ሂደት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ “ከዲፒ ወርልድ ጋር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ፍላጎት ካላቸው ድርጅቶች ውይም ሀገራት ጋር ወደብ የማልማት ተግባር ላይ በትብብር መስራት ትፈልጋለች” ሲሉ አምባሳደር ኦማር ተናግረዋል። 

“እንደዚህ ያሉ ከዲፒ ወርልድ ጋር የሚደረጉ ትብብሮች [ኢትዮጵያ] ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያላትን ጠንካራ አጋርነትን የሚያሳድግ እና ከሌሎች አካላት ጋር ከሚደረጉ ተመሳሳይ ስምምነቶች በበለጠ ጠቃሚ ነው “ ሲሉ አክለው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለውን የንግድ ሁኔታን በተመለከተ አምባሳደሩ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን እና  በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢንቨስት ያሚያደርጉ ኢትዮጵያውያንም እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

ባሳለፈነው ሳምንት በስዊዘርላንድ በዳቮስ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን የዲፒ ወርልድ ሊቀ-መንበርና ሥራ አስፈጻሚ ሱልጣን አህመድ ቢን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የደረጉትን “ውጤታማ” ውይይት ተከትሎ “በርበራ ወደብን ብትብብር ለማልማት ያለንን ቁርጠኝነት ስገልጽ በደስታ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። 

አጋርነቱን “ስትራቴጂካዊ” ሲሉ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው “ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን ከማጠናከር ባለፈ ለዘላቂ ዕድገት መንገድ የሚከፍት ነው” በለዋል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ዲፒ ወርልድ እና ሶማሊ ላንድ የበረበራ ወደብን ለማልማት ስምምነት መፈጸማቸው ይታወሳል። በስምምነቱ መሰረት ዲፒ ወርልድ ከበርበራ ወደ 51 በመቶ ድርሻ የሚያገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ 19 በመቶ፣ ሶማሊያ ደግሞ 30 በመቶ ድርሻ ባለቤት ይሆናሉ።  ነገር ግን ኢትዮጵያ የሚጠበቀባትን ማሟላት ባለመቻሏ ድርሻዋን አጥታለች ስትል ሶማሊ ላንድ አስታውቃለች።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ታህታት 22/ 2016 ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ፤ ለኢትዮጵያ የባህር በር የሚያስገኝ እና በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠት የሚያስችል ስምምነት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። 

ከሁለት ቀናት በፊት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሄ “ በስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለመትልካቸው እና ለምታስገባቸው ክንውኖች የበርበራ ወደብን እንምትጠቀም” ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button