ዜናጤናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የኩዌት የቀዶ ህክምና ቡድን አባላት 500 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ነጻ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4/2015 .ም፡ በኢትዮጵያ አቅም የሌላቸው እና የቀዶ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው 500 በሽተኞች የኩዌት የቀዶ ህክምና አባለት ነጻ አገልግሎት መስጠታቸውን የኩዌት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

አላውን አልሙባሸር የተሰኘ የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር አብዱላህ አልሱማይትን ጠቅሶ የዜና አገልግሎቱ ባሰራጨው ዘገባ በኢትዮጵያ ለአምስት ቀናት የነጻ በጎ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሞያዎችንም ልምድ እንዲቀስሙ መደረጉን ጠቁሟል።

አልአማል የኩዌት የቀዶ ህክምና ቡድን በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ የነጻ ህክምና መስጠት ከጀመረ 13 አመታት መቆጠሩን ዶ/ር አልሱማይት መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በተካሄደው የነጻ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ላይ 21 ዶክተሮችን ጨምሮ 43 አባላት ያሉት የህክምና ቡድን  መሳተፉን የዜና አገልግሎቱ ዘገባ አመላክቷል። በህክምና አገልግሎቱ መስጠት በተጀመረበት እለት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር መታደማቸውንም ዘገባው ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button