ዕለታዊፍሬዜና

ዕለታዊ ዜና፡ በጥንታዊቷ ሀርላ ከተማ ከ6ተኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ኪነ-ህንጻ እና በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13 ዓ/ም፦ በጥንታዊቷ ሀርላ ከተማ ከ6ተኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ኪነ-ህንጻ እና በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች በአርኪዮሎጂስቶች ቁፋሮ መገኘታቸውን የድሬ ዳዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቋል

ጥንታዊ ቅርሶች የተገኙት በፕሮፌሰር ቲሞቲ አሌክሳንደር የሚመራው የሀርላ የአርኪዮሎጂስት ጥናት ቡድን በሀርላ ባደረገው ጥናትና ምርምሮች ነው ተብሏል።

በአርኪዮሎጂካል ቆፋሪዎች ከ 1400 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸው የኪነ-ህንጻ፣ መስጊዶች፣ የጌጣጌጥ መስሪያ ህንጻዎች፣ መቃብሮች ፣ ከኢንዱስትርያል አገልግሎቶች ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ቤቶች (ምናልባትም የልብስ ፋብሪካ ሊሆን የሚችል)፣ በርካታ መኖሪያ ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች መገኘታቸውን የጥናቱ ቡድን መሪ ፕሮፌሰር ቲሞቲ አሌክሳንደር ገልፀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚካኤል እንዳለ፤  “የቅድመ ዘመን ታሪክ ባለቤት የሆነችው ድሬዳዋ ላይ የመካከለኛ ዘመን ታሪክ በሆነው ሀርላ ላይ የተለያዩ ጥናት እና ምርምሮች ተደርገው በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ተገኝተዋል” ብለዋል። 

አቶ ሚካኤል እንዳለ፤ እነዚህን የተለያዩ ተግባራት ይከናወንባቸው የነበሩ ጥንታዊ ቦታዎችን እና በቁፋሮ የተገኙ ጥንታዊ መስጊዶች ለጎብኝዎች በሚያመች ሁኔታ የተዘጋጁ ስለሆኑ በስፍራው በመሄድ መጎብኘት እንሚቻል ተናግረዋል።

ጥንታዊ የሀርላ መንደር የተገነባው በሁለት ዋና ዋና ኮረብታዎች እና ትንንሽ ኮረብታዎች፣ እንዲሁም ወደ ሰሜን አቅጣጫ ተዳፋት ቦታ ላይ በትልልቅ ድንጋዮች በተካቡ ስፍራዎች ላይ ሲሆን በዚህ መንደር ላይም በርካታ የአርኪዮሎጂካል ቆፋሪዎች በተለይም በመኖሪያ ቤቶች ፣ በመቃብር ስፍራዎች እና መስጊዶች ላይ የተለያዩ ጥናቶች ተደርገዋል ተብሏል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button