ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የሶማሊያ እና የኤርትራ መሪዎች 'በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት' ዙርያ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/ 2017 ዓ/ም፦ ቀጠናዊ ውጥረት ባየለበት በአሁኑ ወቅት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ‘በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት’ ዙርያ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በኤርትራ የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ትናንት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ላይ አሥመራ ገብተዋል። አስመራ ዓለምአቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለቱ መሪዎች “በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዋነኝነት በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ላይ ያተኮረ” ውይይት በትናንትናው ዕለት ማድረጋቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል አስታውቀዋል

የማነ ውይይቶቹ በሶማሊያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብርን እንዲሁም የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱ መሪዎች “አስተማማኝ የመከላከያ እና የጸጥታ መዋቅርን ጨምሮ ጠንካራ እና ሉዓላዊ ተቋማትን መገንባት” አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

ውይይቱ የተካሄደው ኢትዮጵያ  ከወደብ ተጠቃሚነት ጋር በተያየዘ ከሶማሌላንድ ጋር የፈጸመችውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረቱ ባየለበት በአሁኑ ወቅት ነው።

ኤርትራ ለሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ሰራዊት ስልጠና ያበረከተችው “መጠነኛ አስተዋጽዖ” እውቅና የተሰጠው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች የሶማሊያን የሀገር ግንባታ ጥረት ለመደገፍ እና በሌሎች ቁልፍ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማስፋት ተስማምተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ጉብኝቱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ እ.ኤ.አ በ2022 ከተመረጡ በኋላ ወደ ኤርትራ ያደረጉት ሰባተኛ ጉብኝታቸው ነው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button