አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም፡- በየካቲት ወር አጋማሽ 2014 ዓ.ም 11 ኮሚሽነሮችን ይዞ ለሶስት አመታት የስራ ጊዜ የተቋቋመው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ አምስት ወራት ቢቀሩትም “አሁን ባለው ሁኔታ የኮሚሽኑ ጊዜ እንዲራዘም አልፈልግም እንዲራዘምም አልጠየቅንም” ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን ገለጹ።
ከሚሽኑ የስራ ጊዜው ሊጠናቀቅ ከአምስት ወራት ያነሱ ጊዜያት በቀሩበት ሁኔታ በትግራይ እና አማራ ክልል ያልጀመራቸውን ስራዎች ጨምሮ ሀላፊነቱን ሙሉ ለሙሉ ማጠናቀቅ ይችላል ወይ? ተብለው በአልአይን የተጠየቁት ዋና ኮሚሽነሩ አስቸጋሪ ይሆናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ “ለአመታት ሲንከባለሉ የመጡ ነገር ግን ለሰላም መደፍረስ እና ግጭት መንስኤ የሆኑ ችግሮችን መለየት እና ወደ መግባባት መድረስ እንደ ኢትዮጵያ ባለ የፖለቲካ እና የሰላም ሁኔታ ውስጥ አስቸጋሪ” እንደሆነ ጠቁመዋል።
ኮሚሽኑ እንዳስፈላጊነቱ በተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል እና እድሜው መሰላት የሚጀምረው ኮሚሽነሮቹ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ መሆኑም በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጁ ላይ ተካቷል።
የኮሚሽኑ ጊዜ የሚራዘም ከሆነ እርሶ በሃላፊነት ይቀጥላሉ ወየ? ተብለው የተጠየቁት ፕሮፌሰር መስፍን “አሁን ባለው ሁኔታ የኮሚሽኑ ጊዜ እንዲራዘም አልፈልግም እንዲራዘምም አልጠየቅንም።” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በእርግጥ የትግራይ እና አማራ ክልሎች ላይ ያሉ ሁኔታዎች ባይዙን ኑሮ ከዚህ ቀደም ብለንም የምንጨርስበት ሁኔታ ነበር፤ ነገር ግን ከሎጂስቲክ ከትራንስፖርት እና ከሰላም ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ስራችንን በተገቢው ፍጥነት እንዳናከናውን እንቅፋት ሆነውብናል፤ አሁን እየሰራን ያለነው በቀረን ጊዜ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ነው እድሜውን የማራዘም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀላፊነት ነው እኔ በግሌ ብጠይቀኝ ግን የኮሚሽኑ እድሜ እንዲራዘም ፍላጎት የለኝም” ብለዋል፡፡
በተመሳሳይፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት የታጠቁ ኃይሎች እና ራሳቸውን ከምክክሩ ያገለሉ ፓርቲዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
“የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም፤ ነገር ግን መሳርያ አስነግቦ ወደ ጫካ ያስወረዳቸውን የፍትሀዊ ተጠቃሚነትንም ሆነ ሌላ የፖለቲካ ጥያቄ አቅርበው በምክክሩ እንዲሳተፉ በተለያየ መንገድ ጥሪ አድርገናል፤ ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል” ብለዋል። አስ