ዜናፖለቲካ

ዜና: የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፣ ኢትዮጵያን እንደማይጎበኙ ተገልጿል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም፡- የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን ከባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ ቀናት ጀምሮ በሀገራቸው ሰላም ማስከበር ሂደት ወታደሮቻቸውን ባሰማሩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ፤ በኡጋንዳ፣ ብሩንዲ እና ጂቡቲ ቅዳሜ እና እሁድ ጉብኝት አካሂደዋል።

የሶማሊያ ፕሬዘዳንት ጉብኝት ኢትዮጵያን አያካትትም ሲሉ ቃል አቀባያቸው አብዱልቃድር ዲጌ መግለጻቸውን ቪኦኤ በዘገባው አስታውቋል።

ፕሬዝዳንቱ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጉብኝታቸውን በኡጋንዳ ካምፓላ የጀመሩ ሲሆን ከፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ሁለቱም መሪዎች የመከሩት በጋራ ጉዳዮች፣ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አትሚስ) ሽግግር ዙሪያ እና ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ መሆኑን የኡጋንዳ መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው አስታውቀዋል።

“ሁለቱም መሪዎች በሶማሊያ እና በቀጠናው ስላለው የጸጥታ ሁኔታ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ማስፈን እንደሚያስፈልግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል” ሲል ከውይይታቸው በኋላ የወጣው የመሪዎቹ መግለጫ አመላክተዋል።

“በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) እና የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች ሀገሪቱን በማረጋጋት እና የሽብር ቡድን የሆነው አልሸባብን ለመዋጋት የከፈሉትን መስዋዕትነት አድንቀዋል” ብሏል።

ፕሬዝዳንት ማሃሙድ በመቀጠል ያቀኑት ወደ ብሩንዲ ሲሆን ከብሩንዲው አቻቸው ኢቫርስቴ ኒዳየሺሚየ ተገናኝተው መክረዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሁለቱ መሪዎች በሀገራቱ መካከል ጠንካራ አጋርነት እንዲኖር ለማስቻል የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን የብሩንዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

“በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ የቡሩንዲ ወታደሮች ያላቸውን ወሳኝ ሚና በመግለጽ የአካባቢውን መረጋጋት ለማረጋገጥ የትብብር ጥረታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበትን መንገድ መክረዋል” ሲል የሶማሊያ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዳውድ አወይስ መግጻቸውን ዘገባዎቹ አካተዋል።

ትላንት ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጂቡቲ የገቡት ፕሬዝዳንት ሼክ ሀሰን በጂቡቲው ጠ/ሚኒስትር አብዲከድር ካሚል አቀባበል እንደተደረገላቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ሼክ ሀሰን ከጂቡቲው አቻቸው ከእስማኤል ጉሌህ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች እንደሚመክሩ የሶማሊያ ዜና አገልግሎት በዘገባው ተጠቁሟል።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ዲጌ በሶማሊያ ቀጣዩ የሰላም አስከባሪ ማን እንደሚካተት በመታየት ላይ ይገኛል ሲሉ መናገራቸውን ቪኦኤ በዘገባው አካቷል።

በቀጣይ ፕሬዝዳንት ሼክ ሀሰን ጉብኝት የሚያካሂዱት ኬንያ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button