Uncategorized

ዜና፡- ለአመታት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት አሰራር መቀየሩን ተቃወሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም፡- ለመኖሪያ ቤት መስሪያ 70 ካሬ ሜትር ይሰጣችኋል ተብለው ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ የመቀለ ከተማ ነዋሪዎች ከአምስት አመት ጥበቃ በኋላ የመኖሪያ ቤት አሰራር ተቀይሯል፣ የሚሰጣችሁ መሬት የጋራ መኖሪያ ቤት መስሪያ ነው መባላቸውን ተቃወሙ።

በመንግስት ድጋፍ ቤታቸውን ለመስራት ለአምስት አመታት ሲጠባበቁ የቆዩት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ገና ጥያቄያቸው እንዳልትፈታና ይልቁን ሌላ አማራጭ እንዲቀበሉ እየተገደዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሮጀክቱን በግለሰቦች እንዲሰራ ከታቀደ G+1 መኖሪያ ቤቶች ወደ ሰባት ፎቅ ህንጻዎች ለማሸጋገር ድንገተኛ ውሳኔ መስጠቱ ተቃውሞ አስነስቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ መስፈርቱን ከሰባት ፎቅ ወደ G+4 ቤቶች ዝቅ በማድረግ አስተካክያለሁ ቢልም፣ የቤቶች ግንባታ ተሳታፊዎች ውሳኔው የዓመታት ቁጠባቸውን የሚያሳጣ እና የረጅም ጊዜ ስምምነትን የሚጥስ ነው ሲሉ ይከራከራሉ።

በተለምዶ “70 ካሬ” በመባል የሚታወቀው ለእያንዳንዱ ተሳታፊ 70 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጥ በገባው ቃል የተሰየመው ይህ ውጥን ከአምስት ዓመታት በፊት በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ መጀመሩ ይታወሳል።

ለሶስተኛ ዙር መርሃ ግብሩ እያንዳንዳቸው 20 አባላትን ያቀፉ ከ3,043 በላይ ማህበራት ተመዝግበዋል።  ተሳታፊዎች በመጀመሪያ 20ሺ ብር በማዋጣት ወርሃዊ ቁጠባ መጀመራቸውና ቁጠባውን መቀጠላቸውን አስታውቀዋል።

ነገር ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከግለሰብ G+1 መኖሪያ ቤት ወደ አፓርታማ ህንፃዎች እንዲቀየር በድንገት መወስኑ ተቃውሞ አስነስቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓም  የማህበራቱ አባላት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ተገኝተው በውሳኔው ቅሬታቸውን ገልፀዋል።  መንግሥት በምዝገባ ወቅት የተደረገውን ስምምነት በመሰረዝ መሬት የማግኘት መብታቸውን መንፈጉን ክስ አቅርበዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ “የሂድሞና ማህበር” አባል እና ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ጋር ለመደራደር የተሰየመው ኮሚቴ አመራር አባል የሆኑት አቶ ካህሳይ አብርሃ በአስተዳደሩ ስምምነቱ መጣስ ቅር እንዳሰኛቸው ይናገራሉ። 

አቶ ካህሳይ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ከጦርነቱ በኋላ ቁጠባ ቢቀጥልም አስተዳደሩ ከጦርነቱ በፊት ለተፈጠሩት እነዚህ ማኅበራት መሬት ለመስጠት የገባውን የመጀመሪያ ስምምነት ጥሷል” ብለዋል።

የትግራይ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ተሳታፊዎች ለቤቶቻቸው መቆጠብ መጀመራቸውን አቶ ካህሳይ አብራርተዋል።

“በጦርነቱና በተፈጠረው የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት መሬቱን ለመቀበል አምስት ዓመታትን ስንጠብቅ ቆይተናል” ብለዋል።

ያጠራቀሙት ገንዘብ እንዴት ዋጋ እንዳጣ ለማስረዳት አቶ ካህሳይ በምዝገባ ወቅት 1 ዶላር በግምት 27 ብር እንደነበር አስታውሰው   “ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የብር ዋጋ በእጅጉ ቀንሷል” ሲሉም አክለዋል።

የክልሉ መንግስት የመጀመሪያውን ስምምነት በመጣስ የተሳታፊዎችን ገንዘብ መያዙን አቶ ካህሳይ ጠቁመዋል።

“በመጀመሪያ G+7 አፓርተማዎችን እንደሚገነቡ ነግረውናል፣ በኋላ ግን ወደ G+4 ዝቅ እንዲል አድርገዋል” ያሉት አቶ አብርሃ መቀሌ የመሬት እጦት እንደሌለባት አፅንኦት ገልጸዋል።  “ከአካባቢው ማዘጋጃ ቤት በተገኘው መረጃ መሰረት የከተማው መሬት አስተዳደር ባለስልጣናት ሰፊ መሬት መኖሩን አረጋግጠው ግን ምደባው በክልሉ መመርያ የሚመራ መሆኑን አስረድተዋል።”

መንግስት በመመሪያ 4/2011 በተገለፀው መሰረት የመኖሪያ ቤት ግዴታውን ባለመወጣቱ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን እንዳሳለፉት አቶ ካህሳይ አሳስበዋል።

አቶ ካህሳይ አያይዘውም “የትግራይ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለጥያቄያችን የሰጠው ምላሽ ትክክለኛ ያልሆነ እና በቂ አይደለም” ብለዋል።

በሶስተኛው ዙር ከተመዘገበው በፊት ፣ የቤቶች መርሃግብሩ ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ዙር ለተጠቃሚዎች ለ G+1 ግንባታ መሬት መስሰጠቱን ።

ሌላው የአመራር ኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ባራኪ ተስፋዬ እንዳሉት ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ​​ለመነጋገር የቤቶች ልማት ተሳታፊዎች በፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት በጅምላ ተቃውሞ ሲያሰሙ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸው  “ነገር ግን እስካሁን ድረስ ምላሽ ሊሰጠን አልቻለም” ሲል በአጽንዖት ተናግረዋል።

አቶ ባራኪም ሆኑ አቶ ካህሳይ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ጊዜያዊ አስተዳደሩ በትግራይ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ እና በቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የ”70 ካር” የራስ አገዝ የቤት ልማት ፕሮግራምን በተመለከተ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ መመሪያ ማውጣቱን ገልጸው   ነገር ግን ይህ አዲስ መመሪያ በምዝገባ ወቅት ከተመሰረተው ስምምነት በእጅጉ የማይጣጣም ነው ብለዋል።

ጉዳዩን ለዓመታት በቅርበት ሲከታተሉት የነበሩት የህግ ባለሙያ አቶ ሀጋዚ ንጉስ በበኩላቸው  እራስ አገዝ መኖሪያ ቤት ውጥኑ የህብረት ስራ ማህበራትን ያካተተ ሲሆን አባላቱን በገንዘባቸው በመጠቀም ባለ አንድ ፎቅ ቤቶችን የሚገነቡበት ነው።

“በመኖሪያ ቤት እጥረት፣ በኑሮ ውድነት እና በሁለተኛ ደረጃ ክፍያ ሳቢያ ለከፋ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየተጋፈጡ መሬትን አግኝተው ለመገንባት እየታገሉ ባሉበት ወቅት፣ የክልሉ መንግስት የመጀመሪያውን መመሪያ  የሚተካ አዲስ አዋጅ በማውጣት ሁኔታውን አባብሶታል። ” ሲሉ ቅሬታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። 

እንደ የህግ ባለሙያው ገለጻ፣ አስተዳደሩ በሚለው  G+4 ግንባታን በሚመለከት ግልጽ መመሪያ የለም፣ ይህም የተገልጋዮቹን ጥቅምና ከትግራይ ጦርነት በፊት ከመንግስት ጋር የተፈራረሙትን ህጋዊ ስምምነት የሚጻረር ነው።

ግንባታው እንዴት እንደሚተዳደር እና ለአፈፃፀም ተጠያቂው ማን እንደሚሆነም የታወቀ ነገር የለም ብለዋል ።

“የቀድሞው ስምምነት ለአፓርትማ ግንባታ የሚሆን ቦታ ስለመስጠት የተናገረው ነገር የለም፣ እና የትኛውም ማኅበራት ለእንደዚህ ዓይነቱ ፕሮጀክት የፋይናንስ አቅም የላቸውም” ብለዋል ። ሆኖም መመሪያው ለ G+1 ግንባታ መሬት አቅርቦት ላይ ትኩረት አድርጓል ።

“መመሪያውን የሚያነሳበት ምንም ምክንያት ስለሌለ መንግስት ይህንን መመሪያ መከተል አለበት” ሲሉም አሳስበዋል።

አቶ ባራኪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት “የፊናንስ ተግዳሮቶቻቸውን በመገንዘብ የክልሉ የቀድሞ መንግስት መመሪያ 4/2011 በማውጣት ለእያንዳንዱ ግለሰብ መጀመሪያ የሚፈለገውን የቁጠባ መጠን ከ48,000 ወደ 20,000 ብር ዝቅ አድርጓል።

አክለውም በፕሪቶሪያ በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የተፈረመውን የጦርነት ማቆም ስምምነትን ተከትሎ ማህበራቱ መመሪያ 4/2011 በማክበር ገንዘባቸውን ማጠራቀም ጀመሩ።

እንደ አቶ ሀጋዚ ገለፃ አዲሱ መመሪያ የቀደመውን ተላልፏል።

“ጊዜያዊ አስተዳደሩ በ2011 መመርያ ላይ ተመስርተው ስምምነት  የፈጸሙ ግለሰቦችን መብት ወደ ጎን መተውን የገለጹት አቶ ሃጋዚ    “አሁን ያለው መመሪያ ከአባላት የፋይናንስ አቅም በላይ የሆነ በጀት የሚፈልግ በመሆኑ ከዚህ በፊት የወጣውን መመርያ እንዲያከበር አሳስበዋል።”

የህግ ባለሙያው ከ80% በላይ የሚሆኑት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውን ጠቁመው አዳዲስ መስፈርቶችን ለማሟላት ፈታኝ ሆኖባቸዋልም ብለዋል።

“በተጨማሪም እስካሁን ያስቀመጡት ገንዘብ ዋጋ ቀንሷል፣ የአፓርታማዎችን ግንባታ ማስተዳደርም  አይቻልም ይህ ትልቅ ተግዳሮት ይፈጥራል፣ እና ለመፈፀም ከአስር አመታት በላይ ሊፈጅባቸው ይችላል።”

የህግ ባለሙያው ምንም አይነት ድንጋጌ ወደ ኋላ ተመልሶ ሊተገበር እንደማይችልምና አዲሱ መመሪያ አግባብ ባልሆነ መንገድ የተነደፈ እና የመኖሪያ ቤት ግንባታ የመሬት አቅርቦትን በሚመለከት መመሪያ 4/2019 የሚጥስ ነው ሲሉ  ይከራከራሉ።  

አያይዘውም “በደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ የማህበራቱ አባላት ያጠራቀሙት ገንዘብ የመግዛት አቅሙን አጥቷል።” ብለዋል።

የትግራይ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አልማዝ ገብረፃዲቅ በቅርቡ ለድምፂ ወያነ እንደተናገሩት የG+1 አፓርትመንት ለመገንባት ካልተስማሙ በስተቀር ለተጠቃሚዎች መሬት አይሰጥም ማለታቸው ተዘግቧል።

አቶ ሃጋዚ ግን ይህንን አቋም ውድቅ በማድረግ የህብረት ስራ ማህበራት እና አባላት የራሳቸውን ገንዘብ ተጠቅመው ባለ አንድ ፎቅ ቤቶችን መገንባት እንደሚችሉ ከሚገልጸው መመሪያ 4/2019 ጋር የሚቃረን ነው ይላሉ

አዲስ ስታንዳርድ ከሃላፊዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። አስ

ተጨማሪ አሳይ
Back to top button