
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5/ 2017 ዓ/ም፦ በመቐለ ውረት መባባሱን ተከትሎ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን የመቐለ ኤፍ ኤም 104.4 እና የከተማዋን ከንቲባ ጽህፈት ቤት መቆጣጠሩን ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
በህወሓት ውስጥ መከፋፈል እና የስልጣን ሽኩቻ እየተባባሰ በመምጣቱ መቐለ፣ አዲግራት እና አዲግደምን ጨምሮ የበርካታ ከተሞች ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።
“ሁኔታው አስፈሪ ነው” ሲሉ አንድ የመቐለ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። “ ቀጥሎ ምን ሊከሰት እንደሚችል አይታወቅም በሚል ፍራቻ ሰዎች ገንዘባቸውን በማውጣትና አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን በመግዛት ላይ ናቸው” ሲሉም አክለዋል።
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ተስፋዬ ገብረመድህን መቀሌ ጸጥታና አመራር ስጋት እንደቀጠለ ነው ሲሉ ተናግረዋል። “በጊዜያዊው አስተዳደር ከንቲባ ተደርገው የተሾሙት አቶ በርሃን ገብረኢየሱስ በስራ ላይ አይደሉም” ብለዋል።
“ይህ በእንዲህ እንዳለ ረዳኤ በርሄ በህወሓት ከተሾሙ ሶስት ወራት በኋላ ትናንት ጽ/ቤቱን ይዘዋል። በደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አሁን መቀሌ ኤፍ ኤም 104.4ን ተቆጣጥሯል” ብለዋል።
በክልሉ ውጥረት ያየለው በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራልምግበይ ሀይለን በግዜያዊነት ማገዱን ተከትሎ ነው። አማራሮቹ በግዜያዊነት የታገዱት “ከመንግስት ውሳኔ ውጭ መላ የክልሉን ህዝብ እና ወጣቱን ወደ ግርግር፣ የጸጥታ ሀይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገባ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ በመሆኑ ነው” ሲል አስተዳደሩ አስታውቋል።
እግዱን ተከትሎ የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ፤ “ውሳኔው ተቋማዊ አሰራርን እና ህግን ያልተከተለ ነው” ሲል እንደማይቀበለው አስታውቋል።
ይህንንም ተከትሎ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆኑትን ሌተናል ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑን ከሃላፊነታቸው አሰናብተዋል። “የቢሮው ሃላፊ ወገንተኝነታቸው የማን እንደሆነ በግልጽ አሳይተዋል” ሲል ተችተዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት “አስፈላጊውን ድጋፍ” እንዲያደርግለት መጠየቁን ተከትሎ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) “በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሶስተኛ ወገን ትግራይ ውስጥ እጁን እንዲያስገባ የሚያደርገው ጥሪ በፍፁም ተቀባይነት የለዉም” ሲል ተዋውሟል።
በክልሉ አለመረጋጋት የተፈጠረው ስጋት ከመቀለ ውጭ ባሉ ከተሞችም እየጨመረ መጥቷል። በደቡብ ምስራቅ ዞን አዲግደምን ከተማ በፀጥታ ኃይሎች እና ጊዜያዊ አስተዳደሩን በሚደግፉ ነዋሪዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ውጥረቱ ከፍተኛ ሆኖ ቀጥሏል፤ በዚህም አምስት ሰዎች ቆስለዋል።
አንድ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው፣ “በመጋቢት 3 ቀን ስድስት የአካባቢው መሪዎች ታስረው ወደማይታወቅ ቦታ ተወስደዋል” ብሏል። ነዋሪው አክለውም “ይህ አይነት ሁኔታ እየተደጋገመ ነው፤ አስተዳደራዊ ለውጦችን የሚቃወሙ ሰዎች ይጠፋሉ፤ ተቃውሞቸውን የሚገልጹ ወጣቶች ዒላማ ይደረጋሉ፤ ብዙዎች በፀጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
“ሰዎች ገንዘባቸውን ከባንኮች እያወጡ ነው” ያለው ሌላኛው ነዋሪ፤ “የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል እናም ፍርሃት ጭንቀት እየፈጠረ ነው” በማለት ሁኔታውን ገልጿል።.
በአዲግራትም ተመሳሳይ ስጋት ያለ ሲሆን ነዋሪዎች የቁጠባ ገንዘባቸውን ለማውጣት በመሯሯጥ እና በባንኮች ረዥም ሰልፍ እየተሰለፉ መሆኑ ተገልጿል። የአዲግራት ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት “የሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ ነው፣ እናም ሰዎች ሌላ እገዳን በመፍራት የቻሉትን ሁሉ እየገዙ ነው። የፖለቲካ አለመረጋጋት ለወጣቶች ሁኔታዎችን አባብሶታል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በአዲስ አበባ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ክልሉ ላይ “የህግ ተቀባይነት ያጡ እና ከጦርነት ትርፍ እናገኛለን የሚሉና በጥቅም የተሳሰሩ የተወሰኑ የህወሃት ቡድን” የተወሰኑ ከፍተኛ መኮንኖችን በመያዝ ክልሉን አደጋ ላይ እየከተቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ እንቅስቃሴ “ትግራይን ወደ ሌላ የትርምስ ምዕራፍ እየወሰደ ይገኛል” ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህንን አስመልክቶ የፌዴራል መንግስት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን እንዲሰራ “ደጋፍ እንዲያደርግ እንጂ ጦር አዝምቶ ጣልቃ እንዲገባ ጥያቄ አላቀረብንም” ብለዋል። በዚህ ደረጃ ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል ሁኔታም የለም ብለዋል።
አቶ ጌታቸው፤ “ክልሉ ወደ ሌላ ጦርነት መግባት የለበትም። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ አካል ነው። የፌዴራል መንግስቱ አግባብነት ያለው ሃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል” ሲሉ ተደምጠዋል። አስ