ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በአገራዊ ምክክር ሂደቱ የማይሳተፍ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11/ 2017 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል የባለድርሻ አካላት ምክክር እየከናወነ ባለበት ወቅት፤ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) በምክክር ሂደቱ የማይሳተፍ መሆኑን አስታውቀ።

ኦብነግ ትናንት ጥቅምት 10 ቀን ባወጣው መግላጫ በሶማሌ ክልል መሪው ፓርቲ ተሳታፊዎችን “በተናጥል መምረጡን፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተደረገውን ስምምነት መጣሱን እንዲሁም ድምጾችን ወደ ጎን ማለቱን” ገልጿል።

ይህም ባላ ድርሻ አካላንት በማሰባሰብ የግጭት መንስዔን ለመፍታት የሚረዳውን ከአገራዊ ምክክር ሂደቱ አላማ የሚቃረን ነው ሲል ከሷል። 

በተጨማሪም ከአማራ፣ ከኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ቁልፍ የፖለቲካ ተዋናዮች ባልተሳተፉበት እና ግጭት በቀጠለበት ምክክሩ መካሄዱ “የአንድ ወገን ብቻ” የመሆን አደጋ እንዳለው እና “እውነተኛ ሰላም እንደማያመጣ” ገልጿል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለሚያመጣ ለእውነተኛ፣ ለአካታች እና ግልጽ ለሆነ ምክክር ቁርጠኛ መሆኑን የጠቆመው ፓርቲው ይህ እንስሚረጋገጥ በአሁኑ ሂደት እንደማይሳተፍ አረጋግጧል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

ከጥቅምት 4-6/2017 ዓ.ም ድረስ በጅግጅጋ፣ በጎዴ እና በዶሎ አዶ ማዕከላት ከ1 ሺ በላይ የማህበረሰብ ወኪሎች ተመካክረው አጀንዳዎቻቸውን መለየታቸውንና 100 የሚሆኑ ወኪሎቻቸውን መርጠው ለባለድርሻ አካላት ምክክር መላካቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የተመረጡት 100 የማህበረሰብ ወኪሎች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የክልሉ መንግስት ተወካዮች፣  የልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች ከትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በአጀንዳዎቻቸው ላይ እየተወያዩ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

አገራዊ ምክክር ሂደቱ ከሀገሪቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች እየገጠመው ያለው ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞም የቀጠለ ሲሆን የካቲት ወር ላይ ኦብነግን ጨምሮ አስራ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያቀፈው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ካውከስ ኮሚሽኑ “አካታች የሆነ አገራዊ ውይይትን የማሳለጥ አላማ አንግቦ ቢመሰረትም አላሳካም” ሲል ተችቷል።

በኦሮሚያ ክልል ዋና የሚባሉት ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በሂደቱ እንደማይሳተፉ ከገለጹ ፓርቲዎች መካክለ ይጠቀሳሉ። በተመሳሳት እናት፣ ኢሕአፓ ያሉ ፓርቲዎችም በምክክር ሂደቱ የማይሳተፉ መሆኑን ማስታወቃቸው ይታወቃል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button