ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የናይጀሪያ አየር መንገድን ለማስጀመር የሀገሪቱ መንግስት የሚያሳልፈውን ውሳኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚቀበል ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያ መንግስት የሀገሪቱን አየር መንገድ ላልተወሰነ ግዜ እንዳይበር ለማድረግም ሆነ ስራ እንዲቀጥል ለማስቻል የሚያቀርበውን ውሳኔ እንደሚቀበል አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስታወቁ።

አየር መንገዳችን የተሳተፈው የናይጀሪያ መንግስት እንድንሳተፍ በይፋዊ ደብዳቤ ስለጠየቀን ብቻ እንጂ ከመጀመሪያውም ፍላጎት ኑሮን አይደለም ማለታቸውን ከበረራ ጋር በተያያዘ ከሚዘግቡ ጋዜጠኞች ጋር በአዲስ አበባ ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄዱት ቃለምልልስ መናገራቸው ተጠቁሟል።

አቶ መስፍን ጣሰው የናይጀሪያ መንግስት የሀገሪቱን አየር መንገድ አስመልክቶ ለሚያስተላልፈው ውሳኔ ተገዢ እንሆናለን ማለታቸውም ተገልጿል። በቅርቡ በናይጀሪያ አቡጃ ከናይጀሪያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መወያየታቸውን ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።

የናይጀሪያ መንግስት ካልፈለገ ለመተው ዝግጁ ነን፤ የናይጀሪያ መንግስት አየር መንገዱን ለማስጀመር ከፈለገ ደግሞ በሀገሪቱ ፍርድ ቤት የተያዙ የህግ ጉዳዮችን ሊጨርስ ይገባዋል ማለታቸውንም ተመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button