ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ ቢመጣ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20/ 2017 ዓ/ም፦ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለጹት ከሁለት ሳምንት በኋላ በሶማሊላንድ ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ ከቢቢሲ ሶማሊኛ አገልግሎት ጋር  ቃለ-ምልልስ ባደረጉበት ወቅት መሆኑን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተከትሎ ውዝግብ መካረሩን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ “ኢትዮጵያ ለምን ከሶማሊላንድ ጋር ስምምነት ተፈራረመች” በሚል የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ “ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ከፈቱ” ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ግብጽ ጣልቃ እንድትገባ መደረጉ ከሶማሊያ በኩል የሶማሊላንድ ሕዝብ የነጻ አገርነት ፍላጎትን ለማስቆም የታለመ ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠቅሰዋል።

“ለ34 ዓመታት ሁለት የተለያየን ነጻ አገራት ነን፤ ሁለት መንግሥታት ነን፤ ሁሉም ያውቀዋል።” ያሉት ሙሳ ቢሂ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ በሶማሊላንድ መሬት የሚመለከታቸው ነገር አለመኖሩን አስረድተዋል።

ይህንን (የሶማሊላንድ ነጻ አገርነት ጉዳይን) በተመለከተም የመግባቢያ ስምምነቱ ከመፈረሙ ቀናት ቀደም ብሎ ለሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጅቡቲ ላይ አግኝተው ነግረዋቸው እንደነበረ አስታውሰዋል።

“ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችበት ስምምነት ምንም ነገር ሳይቀየር በነበረበት እንዳለ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሁሉም ወገን የተግባራዊነት ሰነዱ መቼ እንደሚፈረም በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የስምምነቱ ተግባራዊነት በተመለከተ ሰፊ ጊዜን የሚጠይቅ እና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመቀየር በርካታ ዓመታትን የሚጠይቁ በመሆናቸው መዘግየቱን አንስተዋል።

በሶማሊያ በኩል የተደረገ ጫና በስምምነቱ መዘግየት ላይ ምንም ሚና እንደሌለው የተናገሩት የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት “የመግባቢያ ስምምነቱ የራሱን ጊዜ እየተከተለ ነው። የመጨረሻውን ሁለቱ አገራት የሚወስኑት ይሆናል” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ “ግብጽ በአባይ ወንዝ የተነሳ ከኢትዮጵያ ጋር ለገባችበት ውዝግብ ሶማሊያን እየተጠቀመችባት ወደ ጦርነት ልታስገባት ነው” ሲሉ ከሰዋል።

በተጨማሪም “የራሷ ችግር ያላትን” ግብጽ በቀጠናው እንድትገባ የሶማሊያ መንግሥት መፍቀዱ ስሕተት መሆኑን ገልጸው የሁለቱ ሃገራት (የሶማሊያ እና ግብጽ) ወታደራዊ ስምምነት ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ካለባት ውዝግብ በተጨማሪ በሶማሊላንድ ላይ ጭምር ያነጣጠረ መሆኑን አመልክተዋል።

አክለውም የስምምነቱ ተግባራዊነትን በተመለከተ በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ እጅ ላይ ያለ መሆኑን አስረግጠዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button