ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በመዲናዋ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ መጅሊስ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20/ 2017 ዓ/ም፦ በአዲስ አበባ ከተማ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ።

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አራት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች “በኒቃባቸው ምክንያት” ከትምህርት ገበታ መታገዳቸው በሚዲያዎች ሲሰራጭ ቆይቷል።

ይህን ተከትሎ ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትናንት በጻፈው ደብዳቤ፤ ካለፉት ሁእለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ እንዳንድ ትምህር ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያት “ጫናና እንግልት” እየደረሰ ነው ብሏል።

ችግሩ ለመፍታት ከተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ጋር ስምምነት መደረጉን በዚህም ተማሪዎች ወደ ትህምርት ቤት እንደተመለሱ የገለጸው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ነገር ግን ከቀናት በኋላ ከስምምነቱ በመውጣት ተማሪዎቹ “ማክስ እንኳ አድርገው እንዳይገቡ ተከልከለዋል” ሲል ወቅሷል። 

መጅሊሱ አክሎም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የዲሲፕሊን መምሪያ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ መሆኑን በመጥቀስ “በአንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው አመራሮች ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ መደረጉና የስነልቦታ ጫና መፍጠሩ የህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ-ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት” የሚደረግ ጥረት መሆኑን በመገንዘብ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ሲል ጠይቋል።

በተጨማሪም ተማሪዎቹ “መብታቸው ተጠብቆ” ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button