ዜናፖለቲካ

ዜና: ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባቋቋመው የክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት ለመሳተፍ መወሰኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18/2017 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባቋቋመው ጊዜያዊ ምክር ቤት እንደማይሳተፍ ከአንድ ወር በፊት አስታውቆ የነበረው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ በምክር ቤቱ ለመሳተፍ መወሰኑን አስታወቀ።

በምርጫ ቦርድ እወቅና ተሰጥቶት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባቋቋመው ጊዜያዊ ምክር ቤት እንደማይሳተፍ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

ፓርቲው ትላንት የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባቋቋመው ምክር ቤት ለመሳተፍ መወሰኑን አስታውቋል።

በመግለጫው ላይ የተገኙት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አሉላ ኃይሉ “ጊዜያዊ ምክር ቤቱን የትግራይን ሁለንተናዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መታገያ መድረክ ለማድረግ በምክር ቤቱ በመሳተፍ ለመታገል ወስኗል” ብለዋል።

በጊዜያዊ ምክር ቤቱ ውስጥ “መካተት ያለባቸው ጉዳዮችን በመዘርዘር ሲያመላክት መቆየቱን” የገለጹት የፓርቲው የህገመንግስት እና የህግ ክፍል ሃላፊ የማነ ካሳ በበኩላቸው አብዘሃኛዎቹ ፓርቲው እንዲካተቱ አንስቷቸው የነበሩ ጉዳዮች በጊዜያዊ ክክር ቤቱ መቋቋሚያ ላይ መካተታቸውን አስታውቀዋል።

ፓርቲው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በደረሰበት ውሳኔ መሆኑን ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሙና በይፋ ስራ ማስጀመሩን መጀገባችን ይታወሳል፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አቶ ሞገስ ታፈረን የምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ አድርጎ የመረጠ ሲሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ነጻነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑትነ ደጀን መዝገቦን (ዶ/ር) ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መምረጡ በወቅቱ ተገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ከሲቪል ማህበራት፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ዲያስፖራ፣ የክልሉ ሙሁራን እና የጸጥታ አካላት ተወካዮችን ያካተተ እንደሚሆን ተገልጿል።

ጥር 25 ቀን በተቋቋመው የአማካሪ ምክር ቤቱ ወስጥ ግን የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ ሳልሳይ ወያነ ፖለቲካ ፓርቲ፣ የክልሉ ዲያስፖራ አባላት ተወካዮች አለመሳተፋቸውን በዘገባው መካተቱ ይታወሳል።

ትላንት የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በምክር ቤቱ እንደሚሳተፍ ከገለጸው ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ ውጭ የክልሉ የጸጥታ አካላት እና የክልሉ ዲያስፖራ አባላት ተወካዮች እንስካሁን በምክር ቤቱ እንደሚሳተፉ የገለጹት ነገር የለም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button